አዲስ አበባ —
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ላይ ጉዳት ለማድረስ የለመ ጥቃት ፈፅመዋል ያላቸውን አምስት ሰዎች በሽብር ወንጀል ድርጊት ክስ መሰረተባቸው፡፡ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን መልስ ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ቆርጧል፡፡
በዚሁ ችሎት ፖሊስ በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንትና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ የጀመረው ምርመራ ተጨማሪ አስራ አራት ቀን እንዲሰጠው ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ አሥር ቀናት ብቻ ፈቅዷል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ