በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሙስና በኢትዮጵያ፤ መንስዔና መፍትሔ


የሙስና ገፅታ
የሙስና ገፅታ




please wait

No media source currently available

0:00 0:53:14 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዓለም የሙስና ገፅታ
የዓለም የሙስና ገፅታ
ሙስና በኢትዮጵያ አብዝቶ መንሠራፋቱንና ለዚህም ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች መካከል የሲቪክ ማኅበራት በነፃነት መንቀሣቀስ አለመቻል፣ የመናገርና የፕሬስ ነፃነት መገደብ፣ የሕዝባዊ ተሣትፎ ማነስ እና የመንግሥት ለሕግጋት ተገዥ አለመሆን እንደሚገኙበት አንዳንድ ምሁራን ገልፀዋል፡፡
ፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት ሙስናን ለመከላከል የያዘው ጥረት አበረታች መሆኑንና በዚህ ጥረት ዙሪያም ዜጎች ሁሉ መሣተፍ እንደሚኖርባቸው ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ ሙስና ምን ይመስላል? ምንጩ የት ይገኛል? መፍትሐውስ ምን ይሆን?

ዓለምአቀፉ ፀረ-ሙስና ጥምረት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ባወጣው በአውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር የ2012 ዓ.ም የሃገሮች የሙስና ሠንጠረዥ ላይ ከተፈተሹት ከ174 ሃገሮች ኢትዮጵያ በ33 ነጥብ 113ኛ ቦታን ይዛለች፡፡
የአፍሪካ የሙስና ገፅታ እአአ በ2012 ዓ.ም
የአፍሪካ የሙስና ገፅታ እአአ በ2012 ዓ.ም
ከፍተኛውን የመገምገሚያ ነጥብ 90 ያገኙት የተሻሉ ናቸው ተብለው አንደኛ ቦታን የተቆናጠጡት ዴንማርክ፣ ፊንላንድ እና ኒውዚላንድ ሲሆኑ ዝቅተኛው ስምንት ነጥብ የተሰጣቸው ደግሞ የከፋ ሙስና አለባቸው የተባሉት በሠንጠረዡ ግርጌ በ174ኛነት የሠፈሩት አፍጋኒስታን፣ ሰሜን ኮሪያ እና ሶማሊያ ናቸው፡፡

ቪኦኤ አራት ባለሙያዎችን አወያይቷል፡፡

የመድረኩ ተሣታፊዎች አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር፤ አቶ አበበ ጉታ አዲስ አበባ የሚገኙ የሕግ ጠበቃ፣ አቶ ብርሃኑ አሰፋ በፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነ-ምግባር ትምህርትና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር፣ ዶ/ር ሰዒድ ሁሴን በዩናይትድ ስቴትስ ኬንተኪ ግዛት የመሪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡

ሁሉም ተወያዮች ከተስማሙባቸው የውይይቱ ደንቦች አንደኛው “በሙስና ተጠርጥረው አሁን በቁጥጥር ወይም በጥበቃ ሥር የማገኙት ሰዎች በኢትዮጵያም ሆነ አሜሪካን ጨምሮ በሌሎችም ሃገሮች ሕግጋት መሠረት፣ ከሞራልም አኳያ ጥፋተኝነት ያልተበየነባቸው፣ የፍርዱ ሂደት እስኪጠናቀቅ ድረስም ንፁሃን በመሆናቸው በግልም ሆነ በቡድን ጥፋተኛ ወይም ወንጀለኛ ሊያስመስሏቸው የሚችሉ አስተያየቶችን ከመስጠት መቆጠብ” የሚል ነበር፡፡

ሙሉውን ውይይት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG