በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፍትሕ ሚኒስትሩ ተነሡ፤ የገቢዎች ዳይሬክተር ታሠሩ


አቶ ብርሃን ኃይሉ
አቶ ብርሃን ኃይሉ

በሙስና የተጠረጠሩት ሃያ አራት ናቸው፡፡ የፍትሕ ሚኒስትሩ የተነሡበት ምክንያት አልታወቀም፡፡





please wait

No media source currently available

0:00 0:13:55 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አቶ መላኩ ፋንታ
አቶ መላኩ ፋንታ
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ጥቂት ቀናት በወሰደው እርምጃ አንድ ሚኒስትር፣ ምክትላቸውና ሌሎች ኃላፊዎች በሙስና ተጠርጥረው ታስረዋል።

በቁጥጥር ሥር የዋሉት በሚኒስትር ማዕረግ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፋንታና ምክትላቸው አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ፤ እንዲሁም ሌሎች ኃላፊዎችና ታዋቂ ነጋዴዎች ናቸው።

በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስትር አቶ ብርሃን ኃይሉ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉ ተገልጿል።

ውሳኔው ለሚኒስትሩ የደረሰው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝ ፊርማ ባለበት ደብዳቤ መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ሥልጣን እንዲለቅቁ የተደረገበትን ምክንያት ግን አልገለፁም።

ለዝርዝሩ የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG