ዋሺንግተን ዲ.ሲ —
በቀድሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ፋንታና ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲሁም ባለሃብቶች ላይ የተመሠረተውና በፍርድ ቤት እየታየ ያለው የሙስና ክሥ ለዓርብ፣ ሰኔ 13/2006 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡
ከአንድ ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ከሚገኙት ታሳሪዎች መካከል የስዊድን ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሃኪም ፍቅሩ ማሩ ይገኙበታል።
የዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ቤተሰቦችና የሥራ ባልደረቦቻቸው ከአንድ ዓመት በላይ ያለዋስ መታሠራቸው እንዳሳሰባቸው በመግለፅ አሁን ካሉበት የጤንነት መጓደል የተነሣ አፋጣኝ ፍትህ ያገኙ ዘንድ በስዊድን ሰልፍ አሰናድተዋል፡፡
የስዊድን መገናኛ ብዙኃንም ጉዳዩን እየዘገቡበት ነው።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡