በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ በሽተኛ በኢትዮጵያ


የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሊያ ታደሰ
የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሊያ ታደሰ

የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሊያ ታደሰ የመጀመሪያ የኮሮናቫይረስ በሽተኛ መገኘቱን አረጋግጠዋል።

ቡርኪና ፋሶን ጎብኝተው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የ48 ዓመት ዕድሜ ጃፓናዊ ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

ይህ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት ከ130 በላይ በሚሆኑ ሀገሮች የገባው ወረርሽኝ በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛ በሆነችው ኢትዮጵያ ሊዛመት ይችላል የሚል ሥጋት አሳድሯል።

ኢትዮጵያውያን ቫይረሱ እንዳይዛመት አስፈላጊውን ዕርምጃ እንዲወስዱ ሊያ ታደሰ መክረዋል።

“በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የመጀመርያው የኮሮናቫይረስ በሽተኛ መገኘታቸውን ለማረጋገጥ ችለናል። ስለሆነም ህዝቡ ቀደም ብለን የጀመርነውን የመከላከል ዕርምጃዎችን እንዲወስድ የምንሰጠውን ምክር እናጠናክራለን። የግል ንጽህናን መጠበቅ፣ በተለይም ሲታመሙ ሰዎች ከሚበዙባቸው ቦታዎች መራቅ ያስፈልጋል ብለዋል፤ የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሊያ ታደሰ።

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚደረጉ በረራዎችን የመሰረዝ ዕቅድ እንደሌላትም ገልጸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG