በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቅዳሜው ሰልፍና የፖሊስ እርምጃ


አዲስ አበባ /ፎቶ ፋይል/
አዲስ አበባ /ፎቶ ፋይል/

የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰኘው ተቃዋሚ ስብስብ ከትናንት በስተያ ቅዳሜ (ኅዳር 29/2006 ዓ.ም) አዲስ አበባ ውስጥ የጠራው የአደባባይ ስብሰባና ሰላማዊ ሠልፍ በመንግሥት ታጣቂዎች ተበለተ፣ በእኛም ላይ ድብደባና እሥራት ተፈጸመብን” ብለዋል ተቃዋሚዎች።

please wait

No media source currently available

0:00 0:14:03 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰኘው ተቃዋሚ ስብስብ ከትናንት በስተያ ቅዳሜ (ኅዳር 29/2006 ዓ.ም) አዲስ አበባ ውስጥ የጠራው የአደባባይ ስብሰባና ሰላማዊ ሠልፍ በመንግሥት ታጣቂዎች ተበለተ፣ በእኛም ላይ ድብደባና እሥራት ተፈጸመብን” ብለዋል ተቃዋሚዎች።

የቅዳሜውን የአደባባይ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ከጠሩት ከዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር መካከል አንዱ የሆነው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ ሁኔታውን ለቪኦኤ በስፋት ገልፀዋል። “ወከባና እሥራቱ፣ ብሎም ድብደባው የቆየና ተደጋጋሚ ቢሆንም ታጣቂዎች ከሰኞ ጀምሮ ቢሯችንን ከብበው አናስወጣም/አናስገባም ብለውን ቆይተዋል” ብለዋል።

በሠልፋ ዋዜማ ዐርብ ማታም ከቢሮ በሚወጡት አባሎች ላይ ክትትል በማድረግ የተወሰኑ የፓርቲያቸው አመራር አባላት መታሠራቸውን ገልጸዋል።

የቅዳሜው ስብሰባም ገና ከመጀመሩ ፖሊሶች የመበተን እርምጃ እንደወሰዱና መሪዎቻቸው፤ አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው እንደታሠሩባቸው ገልፀዋል፡፡

ቅዳሜ ለታ በዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር በተጠራው ሰልፍ ላይ በመንግሥት ደረሰ የተባለውን ድብደባና ወከባ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችም አውግዘዋል። ከእነዚህ አንዱ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ነው። «አምባገነኑ የኢሕአዴግ መንግሥት ሰላማዊ ታጋዮችንና በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማሳደዱን አሁንም ቀጥሎበታል» ሲል የሚንደረደረው የአንድነት መግለጫ፣ ቅዳሜ የደረሰውን እርምጃም፣ «አረመኔያዊና ህገ-ወጥ» ብሎታል።

ለዚህ ሁሉ ክስ መንግሥት ምን ይላል? በመንግሥት ኰሚኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ደ-ኤታ አቶ እውነቱ ብላታ ደበላ ካዲሳባ ውጭ አሶሳ በሚካሄደው የብሄረሰቦች በዐል ላይ መሆናቸውን ገልፀው እዚያም ቢሆኑም ግን መረጃ ለመስጠት እንደማይቸገሩ አረጋግጠውልናል። ውይይቱን እንደጀመርን ስልካችን በመቋጡ፣ ለነገ - ማክሰኞ በቀጠሮ ተለያይተናል፡፡

በሌላ በኩል መድረክም ይህን መንግሥት ከትናንት በስተያ ቅዳሜ አደረሰ የተባለውን ድብደባና እሥራት ተቃውሟል፤ መግለጫም አውጥቷል። የሕዝብ ግኙነት ክፍሉ ኃላፊ የዶ/ር መረራ ጉዲናንም መግለጫ አካትተን በሌላ ዘገባ እንመለሳለን፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰልፉ ላይ ታሠሩ ከተባሉት መካከል ዘጠና ሰባት የሚሆኑት በአራዳና ቂርቆስ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃንና የአዲሱ አበበን ዘገባዎች የያዘውን ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG