በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጉጂ ዞን የጸጥታ ችግር ያባባሰው ኮሌራ የሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ መኾኑ ተገለጸ


በጉጂ ዞን የጸጥታ ችግር ያባባሰው ኮሌራ የሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ መኾኑ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:41 0:00

በጉጂ ዞን ዋደራ ወረዳ በተከሠተው የኮሌራ በሽታ፣ ሰዎች እየሞቱ መኾናቸውን፣ ነዋሪዎች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የዋደራ ወረዳ የጤና ባለሞያ፣ በወረዳዋ ከተማ ሳይቀር፣ በበሽታው የተጠቁ በርካታ ሰዎች ሕይወት እያለፈ መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

በአካባቢው ያለው የጸጥታ እና የመጓጓዣ ችግር፣ ኮሌራ በወረርሽኝ ደረጃ እንዲባባስ መንሥኤ መሆኑን የጤና ባለሞያው አስረድተዋል።

የዋደራ ጤና ጽ/ቤት በበኩሉ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገር፣ ኮሌራ በወረዳው በ41 ቀናት ውስጥ ብቻ፣ 10 ሰዎችን ለኅልፈት አብቅቷል፡፡

በአንጻሩ፣ በባሌ ዞኖች ተከሥቶ የነበረው የበሽታው ወረርሽኝ፣ በአሁኑ ወቅት መቀነሱን፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG