በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተቃዋሚዎች በበሬ ወለደ አይክሰሱን - ሃይለማርያም ደሳለኝ


Ethiopian Prime Minister in Native Town for Elections
Ethiopian Prime Minister in Native Town for Elections

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሣለኝ በቦሎሶ ሶሬ ድምፅ ሲሰጡ - ዕሁድ፤ ግንቦት 16/2007 ዓ.ም
ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሣለኝ በቦሎሶ ሶሬ ድምፅ ሲሰጡ - ዕሁድ፤ ግንቦት 16/2007 ዓ.ም

ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ ምርጫ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ሲካሄድ ውሏል።

የዛሬው ምርጫ በሰላማዊና በተረጋጋ ሁኔታ መካሄዱ እየተነገረ ሲሆን፣ ላለፉት 24 ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆየው ገዥው ኢሕአዴግ በዚህ ምርጫ ያሸንፋል ተብሎ ተገምቷል።

በዚህም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እርግጠኛ መሆናቸውን ተንታኞች ይናገራሉ።

የቦሎሶ ሶሬ ድምፅ ሰጭ - ዕሁድ፤ ግንቦት 16/2007 ዓ.ም
የቦሎሶ ሶሬ ድምፅ ሰጭ - ዕሁድ፤ ግንቦት 16/2007 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትውልድ ስፍራቸው አረካ ድምጽ ሲሰጡ ያገኛቸው ሪፖርተራችን ሄኖክ ሰማእግዜር ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኢሕአዴግ የመንግስት ገንዘብና መገናኛ ብዙሃኑን ስለሚጠቀም ለቅስቀሳና ለውድድር አመቺ ሁኔታ የለም ሲሉ ቅሬታ እንደሚያሰሙ አንስቶላቸው በሰጡት መልስ የኢትዮጵያ መንግስት የገንዘብ አጠቃቀምና የሂሳብ አያያዝ ስርአት ግልፅነት በአለም ደረጃ የተደነቀ ነው ብለዋል። በመሆኑም የመንግስት ገንዘብ ለፓርቲ ጉዳይ ብንጠቀም ኖሮ ለጋሾች ገንዘብ አይሰጡንም ነበር፥ ስለዚህ ክሱ የበሬ ወለደ ነው ሲሉ አጣጥለውታል።

XS
SM
MD
LG