በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃውሞ ሰልፍ አዲስ አበባ ላይ ተካሄደ


የተቃውሞ ሰልፍ አዲስ አበባ ላይ ተካሄደ
የተቃውሞ ሰልፍ አዲስ አበባ ላይ ተካሄደ

በዓይነቱ በስምንት ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያ የሆነ የፖለቲካ ተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተካሄደ፡፡ በዚህ ሰልፍ ላይ “ፍትና ነፃነት እንፈልጋለን”፣ “ውሸት ሰለቸን” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ በአዲስ አበባ
ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ በአዲስ አበባ

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:35 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በዓይነቱ በስምንት ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያ የሆነ የፖለቲካ ተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተካሄደ፡፡

በሰማያዊ ፓርቲ በተዘጋጀውና ሌሎችም ፓርቲዎች ድጋፋቸውን በሰጡት በዚህ ሰልፍ የተሣተፉነዋሪዎችም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፤ ፍትሕም ጠይቀዋል፡፡ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ሲካሄድ በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ ሰልፍ ላይ “ፍትና ነፃነት እንፈልጋለን”፣ “ውሸት ሰለቸን” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል፡፡

መሰል ሰልፎችን ለማካሄድ ፍቃድ እየተከለከሉ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሲገልፁ የቆዩ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ተሰምቷል፡፡

የዛሬው ሰልፍ ሊካሄድ የነበረው የአፍሪካ ሕብረት ሃምሣኛ ዓመት በዓል በተከበረበት ዕለት እንደነበረ ይታወሣል፡፡

ከአራት ኪሎ የተነሣው የተቃውሞ ሰልፈኛ በፒያሣ አድርጎ ዋናው ፖስታ ቤት ፊት ለፊት ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው ድላችን ሃውልት ድረስ ተካሂዷል፡፡


የሰልፉ ዓላማዎች አራት መሆናቸውን ለቪኦኤ የጠቀሱት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት እንደሚከተለው ዘርዝረዋቸዋል፡፡
1ኛ - የታሠሩ የፖለቲካ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤
2ኛ - በሚናሩት ቋንቋ ምክንያት ከየመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ወደየቦታቸው ተመልሰው አስፈላጊው ካሣና መቋቋሚያ ተሰጥቷቸው ሰላማዊ ሕይወታቸውን እንዲመሩ በአስቸኳይ እንዲደረግ፣
3ኛ - የሐይማኖት ነፃነታቸው እንዲከበር መንግሥት ጣልቃ እንዳይገባባቸው የጠየቁ የሙስሊሙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤
4ኛ - በመንግሥት የፖሊሲና የአስተዳደር ብልሹነት ምክንያት የተፈጠሩ ሙስና፣ ሥራ አጥነት፣ የኑሮ ውድነት በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲደረግላቸው፤ የሚሉ ናቸው፡፡

አቶ ይልቃል ጌትነት - የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
አቶ ይልቃል ጌትነት - የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

ሰልፉ በሰማያዊ ፓርቲ ይዘጋጅ እንጂ በሃገሪቱ ውስጥ የሚንቀሣቀሱ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ድጋፍ የሰጡት ሲሆን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት- መኢአድ፣ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ - አንድነት፣ የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ኢዴፓና የሌሎችም ፓርቲዎች አመራር አባላት በሰልፉ መገኘታቸው ታውቋል፡፡

ከአዲስ አበባ የተቀናበረውን የእስክንድር ፍሬው ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG