በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአርሲ ኮፈሌው ግጭት ሕይወት ጠፋ


ኮፈሌ
ኮፈሌ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:43 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:35 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አርሲ ውስጥ በኮፈሌ ወረዳ ከትናንት በስተያ ቅዳሜ እና ዕሁድ በተቀሰቀሱ የሙስሊሞች ተቃውሞዎችና በተከተሉት ግጭቶች ቢያንስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ምሥክሮች ገለፁ፤ የመንግሥት ባለሥልጣናቱ በተፈጠረው ግጭት የተገደሉት ሰዎች “ሦስት ናቸው” ይላል፡፡

የፀጥታ ኃይሎች በኮፈሌ ወረዳ መንገድ ላይና የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ ሰዎችን በማሰር ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቪኦኤ አስታውቀዋል።

የአካባቢው ፖሊስ ባልደረባ የታሠሩ ሰዎች መፈታታቸውንና የፀጥታው ሁኔታ መረጋጋቱን ገልፀዋል።

ቅዳሜ ዕለት ከኮፈሌ ከተማ 25 ኪሎሜርት ርቀት ላይ ባለች አነስተኛ የገጠር ቀበሌ የሚገኝ መስጊድ ኢማምን ለማሰር የተደረገ ጥረት ወደ ሁከት እንዳመራ የዐይን ምስክሮች ይናገራሉ።

ምስክሮቹ ወሬው ወደ ትናንሽ የገጠር ከተሞች በፍጥነት ደርሶ ህዝቡ ተቃውሞ ማሰማት እንደጀመረና ግጭትም መፈጠሩን ይናገራሉ፡፡

በኮፈሌ ከተማም እንዲሁ ግጭት ተፈጥሮ በአጠቃላይ በወረዳው እስካሁን ስማቸው የተረጋገጠ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ሲጠቅሱ የሟቾቹ ቁጥር ግን በአሥራዎቹና ከዚያም በላይ ሊሆን እንደሚችል ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ግጭቱ የተከሰተው የፖሊስን ሥራ ለማስተጓጎልና የሽብር ሥራ ለማድረስ በተንቀሳቀሱ አካላትና በፀጥታ ሀይሎች መካከል ነው ይላል። በፖሊስ ላይ በፈንጂ ጉዳት ማድረሣቸውንም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ፈንጂውን ማን እንዳፈነዳው ግን የታወቀ፤ ወይንም ይፋ የሆነ የምርመራ ማስረጃ አልተገኘም። የአካባቢው ነዋሪዎች ግን “የፈነዳ ፈንጂ የለም” ብለዋል ለቪኦኤ።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG