በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ክልል የረቡዕ ውሎ


ሰሞኑን የሥራ ማቆም አድማ ተደርጎ በነበረባቸው በጎንደርና በደብረ ማርቆስ ከተሞች ሰዉ ዛሬ፤ ረቡዕ ወደ ሥራ እየገባ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የአማራ ክልል የረቡዕ ውሎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:23 0:00

ሰሞኑን የሥራ ማቆም አድማ ተደርጎ በነበረባቸው በጎንደርና በደብረ ማርቆስ ከተሞች ሰዉ ዛሬ፤ ረቡዕ ወደ ሥራ እየገባ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በጎንደር መሥሪያ ቤቶች ክፍት ቢሆኑም አገልግሎት ሰጭዎች ግን ዛሬም ሥራ አለመጀመራቸውን ቪኦኤ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ የከተማው ከንቲባ ከአገልግሎት ሰጭዎች ጋር መወያየታቸውንና በቅዳሜው ሰላማዊ ሰልፍ ምክንያት የታሠሩ ሰዎች መለቀቃቸውን አንድ የከተማዪቱ ነዋሪ ገልፀዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ነዋሪዎች ከባለሥልጣናቱ ጋር ተሰብስበው በነበረበት ወቅት ያነሷቸው ጥያቄዎች “የታሠሩ ልጆቻችን ይፈቱ፤ ከሌላ አካባቢ የመጣ ኃይል ይውጣ፤ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ መልስ ይሰጠው” የሚሉ እንደነበሩም ነዋሪው አመልክተው በውይይቱ ያልተደሰቱ ስብሰባውን ረግጠው የወጡ ተሣታፊዎችም እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡

የክልሉን የዛሬ ውሎ አስመልክቶ ከመንግሥቱ ባለሥልጣናት ማብራሪያ ለማግኘት የተደረጉ ተከታታይ ሙከራዎች ባይሳኩም የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ቀደም ሲል ለቪኦኤ ሰጥተውት በነበረ መግለጫ ግን “መንግሥት ከየአካባቢው ነዋሪዎች ጋር እየተመካከረ መሆኑን፤ እንቅስቃሴዎቹን የሚያደርጉት የክልሉን ደኅንነት ለማወክ የሚፈልጉ ፀረ-ሰላም ኃይሎች መሆናቸውን፤ ሕገ-መንግሥታዊውን ሥርዓት በኃይል ለመጣል የሚሞክሩ ኃይሎችን አግባብ ባለው መንገድ ለመመከት እንደሚንቀሳቀስ” ገልዋል፡፡

ለሙሉው ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG