በአማራ ክልል መዘዞ ከተማ ታጣቂዎች አንድ የፖሊስ ጣቢያን ለተወሰነ ሰዓት ተቆጣጥረው መሣሪያ መውሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቪኦኤ አስታውቀዋል።
ክልሉ ውስጥ ሰሞኑን የተስተዋለው በነዋሪዎችና በፌዴራል ሠራዊት መካከል ያለው ግጭት የጀመረው ባለፈው ሳምንት ሲሆን ይህም መንግሥት የክልሎች ልዩ ኃይሎች ፈርሰው ከፌዴራል መከላከያ ኃይሎችና ከፖሊስ ጋር እንዲቀላቀሉ መመሪያ ማስተላለፉን ተከትሎ የመጣ ነው።
በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ውስጥ የተኩስ ልውውጥ እንደነበረና የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የቪኦኤዋ ማያ ምሥክር ከአዲስ አበባ ያጠናቀረችውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።