በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትግበራ ፍሬ እያፈራ ነው ተብሏል


በኢትዮጵያ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትግበራ ፍሬ እያፈራ ነው ተብሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:57 0:00

በኢትዮጵያ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትግበራ ፍሬ እያፈራ ነው ተብሏል

በርካታ ተቋማት ሰው ሰራሽ ልሕቀት ቴክኖሎጂ በመጠቀም አገልግሎታቸውን በማዘመን ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ገልጿል።

የኢንስቲቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና፣ አርተፊሻል ኢንተሊጀንስን በመጠቀም የአገልግሎት ዘርፋቸውን ሙሉ በሙሉ የቀየሩ ተቋማት እንዳሉ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ለ2 ቀናት በተካሔደው 3ኛው የፓን አፍሪካ ኤአይ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ሰው ሰራሽ ልሕቀት ቴክኖሎጂከሌላው ዓለም ይልቅ ለአፍሪካ እጅግ አስፈላጊ ቢሆንም በአህጉሪቱ ተግባራዊነቱ ዝቅተኛ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት የሰው ኃይል እና የመሰረተ ልማት ችግር እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ አፍሪካውያን የዘርፉን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ በጋራ መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG