በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሣይንሶች አካዳሚ ዕውቅና አገኘ፤


Academy of Sciences of Ethiopia
Academy of Sciences of Ethiopia

የኢትዮጵያ ሣይንሶች አካዳሚ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወጣ ሕግ ዕውቅና አገኘ፡፡






የኢትዮጵያ ሣይንሶች አካዳሚ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወጣ ሕግ ዕውቅና አገኘ፡፡

የወጣው ሕግ የተረቀቀው በአካዳሚው እንደሆነና በምክር ቤቱ የፀደቀው ሕግም ለተቃውሞ ሙሉ ነፃነት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

/ዘገባው በድምፅ ተያይዟል፤ ያዳምጡት/

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:52 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


The Milky Way
The Milky Way
ባማረውና በጠራው ሌሊት አፍሪካ ላይ ሆነው ወደ ሰማይ ቢያስተውሉ የሚመለከቱት በእኛይቱ ፀሐይና በዙሪያዋ ያሉ ፕላኔቶች ሚልኪ ዌይ የሚባለው የዑደት ሥርዓት ወይም ጋላክሲ እምብርት እንደሆነ ያውቁ ይሆን? አፍሪካ ይህንን የእኛን ጋላክሲ ወይም ሚልኪ ዌይን ለማየትና ለመከታተል እጅግ የተመቸ ገዥ መሬት ነው በምድር ላይ የተቆናጠጠችው፡፡

አፍሪካ ግን በጠፈር አሰሣና ምርምር እምብዛም ስትታማ አይሰማም፡፡ በአውሮፓ አቆጣጠር በ1960ዎቹ የነበረው የኅዋ እሽቅድምድም ተሰላፊና ተጋፊም አልነበረችም፡፡

አሁን አሁን ግን የሰማይ ምርምርና የጠፈር መርኃግብሮች ከዚህ ሠፈራችንን ከከበበው የቅርቡ ሁለንተና ባሻገር በጥልቁ ቀላይ ውስጥ ምን እየተከናወነ እንደሆነ ሊያስተምሩን እየማሰኑ ነው ይላል ፒተር ኮክስ ከጆሃንስበርግ የላከልን ዘገባ፡፡

ዓለም በጨለማ ከሰማይ ሲያይዋት
ዓለም በጨለማ ከሰማይ ሲያይዋት
ኬፕ ታውን የሚገኘው የከዋክብት ሣይንስ ዓለምአቀፍ ቢሮ የደቡብ አፍሪካ የከዋክብትና የሰማይ አካላት ቃፊር ፅሕፈት ቤት ዳይሬክተር ኬቭን ጎቬንደር ኅዋን ለመቃኘት አፍሪካ የተመቸች አህጉር መሆኗን ይናገራሉ፡፡
XS
SM
MD
LG