በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ከእሥልምና ጋር እየተዋጋች አይደለችም - ፕሬዚዳንት ኦባማ /ውይይት በቪኦኤ/


አሜሪካ ከእሥልምና ጋር እየተዋጋች አይደለችም - ፕሬዚዳንት ኦባማ
አሜሪካ ከእሥልምና ጋር እየተዋጋች አይደለችም - ፕሬዚዳንት ኦባማ

በዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በተዘጋጀው ዓለምአቀፍ ስብሰባ ላይ ከአቶ ተሾመ ብርሃኑ (ከኢትዮጵያ)ና ከዶ/ር አሕመድ ሞኤን (ዋሺንግተን ዲሲ) ጋር የተካሄደ ውይይት፤ ክፍል አንድ እና ሁለት፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:40:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:37:03 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በተዘጋጀው ዓለምአቀፍ ስብሰባ ላይ የተናገሩት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ “…ሁላችንም የአንዲት ጀልባ ተሣፋሪዎች ነው፤ ከወጀቡ ለመውጣትም አብረን መታገል አለብን…” ብለዋል፡፡

“ሁከተኛ ፅንፈኝነትን መጋፈጥ” በሚል ርዕስ የተካሄደው ይህ ስብሰባ የስድሣ ሃገሮች ልዑካን የተገኙበት ሲሆን የሽብርና የፅንፈኝነትን ሥር ወመሠረት ለመፈተሽ የታሰበ ነው፡፡

ስብሰባውን በንግግር የከፈቱትና የዘጉት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ “አሜሪካ እየተዋጋች ያለችው ከጥላቻ አስተሳሰቦች ጋር እንጂ ከእሥልምና ጋር አይደለም” ብለዋል፡፡

አቶ ተሾመ ብርሃኑ
አቶ ተሾመ ብርሃኑ

በዚህ ስብሰባ አካሄድና በተነሱ አንዳንድ ነጥቦች ላይ ሃሣቦቻቸውን እንዲያካፍሉን ምሁራንና ለጥያቄው ቅርበት ያላቸውን ሰዎች ጋብዘናል፡፡

በውይይቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ የተሣተፉት ኢትዮጵያ ያሉት የታሪክ፣ የማኅበራዊ ግንኙነቶችና እሥልምና ተመራማሪና ፀሐፊ አቶ ተሾመ ብርሃኑ እና ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ የኅብረተሰብ ጤና ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር አሕመድ ሞኤን ከፕሬዚዳንቱ ንግግር ጋር ይስማማሉ፡፡

አሕመድ ሞኤን (ዶ/ር)
አሕመድ ሞኤን (ዶ/ር)

ዶ/ር አሕመድ “…እንዲያውም ይህንን ለማለት ፕሬዚዳንቱ በጣም ዘግይተዋል…” ብለዋል፡፡ አቶ ተሾመ ደግሞ “…ይህ የፕሬዚዳንቱ አቋም በሙስሊሙ ዓለም እና በሙስሊሞች በአንድ ወገን፤ በሌላ ደግሞ በአሜሪካ መካከል አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ የሚከፍት ነው …” ብለዋል፡፡

ሁለቱም ምሁራን የአሜሪካና የኢትዮጵያን ሚድያዎች በሙስሊሙ ዓለም ውስጥ እየታዩ ያሉ ሕፀፆችን ከልክ በላይ አጋንነው እያቀረቡ በሰዉ ውስጥ እሥላምን የመፍራት ወይም የመጥላት ወይም የመጠርጠር ስሜት እንዲፈጠር እያደረጉ ናቸው ሲሉ ይወቅሳሉ፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ “እሥላማዊ መንግሥት” ቡድንን በመሳሰሉ ድርጅቶች እየተፈፀሙ ያሉትን የጭካኔ አድራጎቶች ግን እሥላማዊ አይደሉም ሲሉ ኮንነዋል፡፡

በሁለት ክፍሎች የተላለፈውን ውይይት ከተያያዙት የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG