በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዙን አስታወቀ


አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/

የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ቁጥጥሩ ሥር እንደሚገኙ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዙን አስታወቀ

የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ቁጥጥሩ ሥር እንደሚገኙ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ፡፡

በመንግሥቱ ቴሌቪዥን የቀረበው ዜና “አንዳርጋቸው ላለፉት አምስት ዓመታት በተለያዩ ስሞች ኤርትራ ውስጥ መሽጎ ከሻዕቢያና ከሌሎች ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች ጋር በመቀናጀት አሸባሪዎችን በማስተባበር እና በማሠልጠን የሃገራችንን ሰላም ለማደፍረስና ልማቷን ለማደናቀፍ ጥረት ያደርግ እንደቆይ ይታወሣል” ይላል፡፡

ዜናው አቶ አንዳርጋቸው “እረፍት ብቻ እፈልጋለሁ፤ በጣም ደክሞኛል፤ ልቤ ውስጥ ምንም ዓይነት ቂም የለም” ሲሉ አሳይቷቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከግንቦት ሰባት እና ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ሲተባበሩ ነበሩ የተባሉ ሌሎች ሰዎች በፍርድ ቤት ተዕዛዝ ዛሬ ሐምሌ 1/2006 ዓ.ም በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG