በሥርዓተ ቀብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ፥ ሚኒስትሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተወካዮችና የየማህበረሰቡ ተጠሪዎች ተገኝተዋል።
መስቀል አደባባይ ላይ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ መንግሥት ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ሱዛን ራይስ፣ የቤኒን ፕሬዚዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ዶክተር ቦኒ ያዬ ንግግር አድርገዋል።
የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ፣ የርዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጄከብ ዙማና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዴትም እንዲሁ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚዘክሩ ንግግሮችን አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በገጠማቸው የጤና እክል በውጭ ሀገር በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በ 57 ዓመታቸው ያረፉት ነሐሴ 14 ቀን 2004 ዓ.ም መሆኑ በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን መነገሩ ይታወሣል፡፡
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡