ውዝግብ ባስነሳው ፈተናዎች ውጤት ላይ ትምሕርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጠ
ውዝግብ ባስነሳው ያለፈው ዓመት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ውጤቶች ጉዳይ ላይ መግባባት ላይ መደረሱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቀዋል። በሌላ በኩል ግን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር አለመነጋገሩን ቅሬታና ሥጋታቸውን በይፋ ካሳወቁት መካከል የሚገኘው የሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም አመልክቷል። አሁንም ጥያቄዎች እንዳሉ ዋና እምባ ጠባቂው ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ተናግረዋል። የፈተና ሥርቆት ዋነኛ ችግር መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለእንደራሴዎቹ ገልፀዋል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ሜይ 19, 2022
ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባህርዳር እንደሚገኙ ጠበቃቸው ገለፁ
-
ሜይ 19, 2022
የትግራይ ክልል መንግሥት የጦር ምርኮኞች እንዲለቀቁ መወሰኑን አስታወቀ