በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመላ አፍሪካ የወንጀል ጉባዔ ባሕርዳር ላይ እየተካሄደ ነው


ሲናይ
ሲናይ



ሲናይ
ሲናይ

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አፍሪካ ውስጥ ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ እና ለሕገወጥም ጉዳዮች ማሸጋገር፣ መድኃኒቶችን፣ ማዕድናትን፣ እንደዝሆን ጥርስ የመሣሰሉ የተከለከሉ አደኖች ውጤቶችንና ሌሎችም ሃብቶችና ሸቀጣሸቀጥ በሕገወጥ መንገድ ማንቀሣቀስና ማስተላለፍ ሁል ጊዜ ችግር ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

መንግሥታቸውን እየሸሹ በሚጠፉ ኤርትራዊያን ላይ እየተፈፀመ ነው የሚባለው አዲስ ዓይነት ንግድ ግን ቀድሞ ያልታየ አስፈሪና ዘግናኝ አድራጎት ታሪኮችን ፈጥሯል፡፡
የሲናይ ቁስል
የሲናይ ቁስል

ኤርትራዊያኑ ስደተኞች ሱዳን ውስጥ ተጠልፈው ወደ ግብፅ ይሸጡና ቤተሰቦቻቸው ቤዛ የሚሆን ገንዘብ እስኪልኩ በስቃይ ውስጥ እንዲቆዩ ይደረጋሉ፡፡

ባሕርዳር
ባሕርዳር

ይህንንና መሰል ኢሰብአዊና ድንበር አቋራጭና የተደራጁ የወንጀል አድራጎቶችን አንስቶ የሚመክር የመላ አፍሪካ ጉባዔ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሕርዳር ከተማ ላይ እየተካሄደ ነው፡፡

ሜሮን እስጢፋኖስ
ሜሮን እስጢፋኖስ

ሜሮን እስጢፋኖስ በባሕርዳሩ ጉባዔ ላይ ለመሣተፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የኤርትራ ተወላጅዋ ስዊድናዊት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ሜሮን በቀን ከ15 እስከ ሃያ የሚደርሱ ኤርትራዊያን ስደተኞችን የስልክ ጥሪዎች ይቀበላሉ፡፡ ስብሰባው እየተካሄደ ሣለ ከቪኦኤ ጋር ለመነጋገር ወጣ ያሉ ጊዜ የእጅ ስልካቸውን ሲመለከቱት የተደረደሩት ያመለጧቸው ወይም ያልመለሷቸው ስልኮች ብዛት ያስደነግጥ ነበር አለች፤ የዚህ ዘገባ አጠናቃሪ ሃና ማክኔሽ፡፡

ሜሮን የሚያነጋግሯቸው ብዙዎቹ ኤርትራዊያን የሚደውሉት በሚደርስባቸው በጠላፊዎቻቸው ወይም በገዥዎቻቸው በሚደርስባቸው ሥቃይ መከራቸውን እያዩ ነው፡፡

“እያሰቃዩሽ ቤተሰቦችሽ ወይም ወላጆችሽ ጋ ይደውላሉ፡፡ እኔ ከአንዲት ልጅ እናት ጋር ተነጋግሬ ነበር፡፡ ልጅዋ በአምስት ወንዶች ስትደፈር እንድትሰማ ያደርጉ ነበር፡፡ የማስለቀቂያው ክፍያ ከሰላሣ ሺህ እስከ ሃምሣ ሺህ ዶላር ይደርሣል፡፡ አማራጭ ስታጣ፣ ካለህ ትከፍላለህ፤ ካለበለዚያም ትሞታለህ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አድራጎት እየተፈፀመ ያለው እአአ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ግን እያየ እንዳለየ መሆንን መርጧል፡፡” ብለዋል ሜሮን እስጢፋኖስ፡፡
ሲናይ
ሲናይ

እሥራኤል የአፍሪካዊያን ስደተኞችን የሥራ ፍቃድ በመንጠቋና ዓለምአቀፍ ለጋሾች ደግሞ ወደአውሮፓ የሚነጉደውን የስደተኛ ማዕበል ገታ እንዲያደርጉላቸው ለቀድሞው የሊብያ መሪ ሙአማር አል ከዛፊ ሰጥተው ስለነበረ ቀደሞ ሕገወጥ አስተላላፊ የበሩት አሁን የተያያዙትን አዲሱን ዓይነት የሥቃይ ንግድ ጀመሩና ገበያውንም አደሩት፡፡
ከሲናይ የእሥርና ማሰቃያ ሠፈሮች አንዱ
ከሲናይ የእሥርና ማሰቃያ ሠፈሮች አንዱ

ድንበር እያቋረጠ የሚያመልጥ ዜጋ ቢገኝ ተኩሶ የሚገድለውን የኤርትራን መንግሥት እየሸሹ ከሃገር የሚጠፉ ኤርትራዊያን ቁጥር በወር ወደ ሦስት ሺህ እንደሚደርስ አንድንድ የረድዔት ድርጅቶች ይናገራሉ፡፡
ከሲናይ የእሥርና ማሰቃያ ሠፈሮች አንዱ
ከሲናይ የእሥርና ማሰቃያ ሠፈሮች አንዱ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር - ዩኤንኤችሲአር እንደሚለው በመላ አፍሪካ ቀንድ ውስጥ ከሩብ ሚሊየን በላይ ኤርትራዊያን ስደተኞችና ወደ 15 ሺህ የሚሆኑ ደግሞ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች ይገኛሉ፡፡

የኤርትራ መንግሥት ዜጎቹ ከሃገር ለመውጣታቸው እንዲከፍሉ ያደረጋል እየባለ ይወቀሣል፡፡ ሸሽተው የወጡ ሰዎችን ቤተሰቦች እንደሚቀጣ፣ በውጭ ሃገሮች የሚገኙ ኤርትራዊያን ከገቢያቸው 2 ከመቶ ታክስ እንዲከፍሉ በገሃድ የማይታዩ ግን አስገዳጅ የሆኑ ዘዴዎችን እንደሚጠቀም ይነገራል፡፡
ሲናይ
ሲናይ

ተደጋግሞ እንደሚሰማውና ዓለምአቀፎቹ ድርጅቶችም እንደሚሉት ብዙ ኤርትራዊያን ሱዳን ውስጥ ከሚገኙ የስደተኛ መጠለያ ሠፈሮች እየታፈኑና እየተጠለፉ ግብፅ ውስጥ ላሉ በደዊኖች ለሚባሉ የተለያዩ ጎሣዎች አባላት ይሸጣሉ፡፡

ከስዊድን የፖለቲካ ወገናዊነት የሌለው የኤርትራ ዜና የራዲዮ ሥርጭት ሥራ የሚያካሂዱት ሜሮን እስጢፋኖስ ሁሉም እጁን አጣጥፎ ባለበት ሁኔታ እጅግ ዘግናኝ የሆኑ የጭካኔ አድራጎቶች እንደሚካሄዱ ይናገራሉ፡፡ “በየቀኑ ለአራት ሰዓታት እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ቸንክረው ይሰቅሏቸዋል፡፡ ወንዶቹንም ሴቶቹንም በቡድን ይደፍሯቸዋል፡፡ ታጋቾቹ እርስ በራሣቸውም እንዲደፋፈሩ ያስገድዷቸዋል፡፡” ብለዋል ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፡፡

“በሺሆች የሚቆጠሩ በእንዲህ ዓይነት ጠለፋና ሥቃይ ውስጥ አልፈዋል” የሚሉት ሜሮን ወደ መቶ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ አሁንም በጠላፊዎቹ እጆች ውስጥ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡
የሲናይ ጠባሣ
የሲናይ ጠባሣ

በአፍሪካ ቀንድ የአውሮፓ ኅብረት ተጠሪ አሌክሣንደር ሮንዶስ “ይህ ዓለም ሊነቃበት የሚገባ ችግር ነው” ይላሉ፡፡ “ለምን እንዲህ ዓይነት ይደረጋል ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ እንዲህ ዓይነት አስፈሪና ቀፋፊ ነገር አሁን እየተፈፀመ መሆኑን መረዳት ይከብዳል፤ ይህ ዓይነተኛ የፍፁም ግድየለሽነት መገለጫ ነው፡፡” ብለዋል ሚስተር ሮንዶስ፡፡

የዚህ “ዝም የተባለበት አሣዛኝ ታሪክ” ሲሉ ሮንዶስ የጠሩት አድራጎት ወሬ “በዓለም ሁሉ መናኘት፣ ለዓለም ሁሉ መሰማት አለበት” ብለዋል፡፡
በሲናይ የበደዊኖች መንደር
በሲናይ የበደዊኖች መንደር

“ሰዎች ይህንን ታሪክ ከነ ሙሉ ዘግናኝነቱ ወይም አስፈሪነቱ ነው ማወቅ ያለባቸው፡፡ ይህ እራሱን የቻለ የባርያ ንግድ ዓይነት ነው፡፡ ቁጥሩ ሊገለፅ የማይችል ገንዘብ የባሕር ላይ ውንብድናን ወይም ፓይረሲን ለማስወገድ እናፈስሣለን፡፡ ይህኛው ግን እጅግ የባሰ በሰው ሕይወት ላይ የሚመነዘር በርካታ መዘዝ ያለው የውንብድና ዓይነት ነው፡፡” ሲሉ አክለዋል የአውሮፓ ኅብረቱ ተጠሪ፡፡

ሰዎቹ በብዙ ሃገሮች ውስጥ እያለፉና እየተሸጋገሩ ሕገወጥ ማስተላለፍንና የሰው ንግድን ለማስወገድ አንዳች እርምጃ ያለመወሰዱ የሚያሣየው አንዳች የተቀነባበረ የሙስና ሴራ ሊኖር የመቻሉን ነገር ነው ይላሉ የአውሮፓ ኅብረቱ ሮንዶስ፡፡
የሲናይ እንባ
የሲናይ እንባ

በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ንግድ የሚካሄደው በሃያ አምስት ቤተሰቦች ወይም ጎጦች መሆኑንና በፍጥነት ማጥፋት የሚቻል መሆኑን ሜሮን አመልክተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት አንድ የተጠለፈ እንግሊዛዊን ለማስለቀቅ በሲናይ ላይ ወረራ አካሂደው እንግሊዛዊውን ያስለቀቁት የግብፅ የፀጥታ ኃይሎች በሰንሠለት የታሠሩ፣ የተደበደቡ፣ በረሃብ የደከሙ፣ የጭካኔና የሥቃይ አያያዝ እየተፈፀመባቸው እንደነበረ በግልፅ የሚታዩ ሌሎች ሰዎችን አግኝተው ሣያስለቅቋቸው መመለሳቸውንም ሜሮን ገልፀዋል፡፡
የሲናይ እንግልት
የሲናይ እንግልት

ይህ የኤርትራዊያኑ መጠለፍ ጉዳይ ትልቅ ችግር መሆኑን የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል በሽር በዚሁ የኢትዮጵያው የወንጀል ጉዳይ ጉባዔ ላይ ማመናቸው ተዘግቧል፡፡

በግብፅም የወደቀው የሙባረክ አስተዳደር ባለሥልጣናት የበኩላቸውን እገዛ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተው እንደነበረ ተጠቁሟል፡፡

አራት ዓመታት ካለፉ በኋላ ግን ችግሩ ተወግዶ አልታየም፤ እንዲያውም በዓለም ገፅ ላይ እጅግ በበረታ ድኅነት ውስጥ የሚማቅቁ ሕዝቦች በሚኖሩበት ጥግ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ይህ ከመከራ የመገላገያ ቤዛ ክፍያ በብዙ እጅ አሻቀበ እንጂ፡፡
የሲናይ አሻራ
የሲናይ አሻራ

ይህ ስቃይና የሰው ልጅ መከራ ፍፃሜው ቅርብ እንዲሆን ብዙዎች ተስፋቸውን እየገለፁ ነው፡፡
XS
SM
MD
LG