በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራውያን ስደተኞች አምልኮ በአዲስ አበባ


የኤርትራውያን ስደተኞች አምልኮ በአዲስ አበባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:35 0:00

ኤርትራውያንን ለስደት ከሚዳርጓቸው ምክንያቶች አንዱ በሀገራቸው የእምነት ነፃነት አለመኖር እንደሆነ ቪኦኤ በአዲስ አበባ ያነጋገራቸው አንድ የኃይማኖት አገልጋይ ተናግረዋል፡፡ የፕሮቴስታን እምነት ተከታዮች በሀገራቸው በነፃነት የማምለክ መብት እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡

አሁን ግን በስደት በሚኖሩበት አዲስ አበባ በነፃነት እንደሚያመልኩ ገልፀዋል፡፡ በአዲስ አበባ እስከ 30 ሺህ የሚገመቱ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኤርትራውያን ስደተኞች መኖራቸውን እና ለነሱ በትግርኛ አገልግሎት የሚሰጡ አብያተክርስቲያን እንዳሉ አገልጋዩ ይገልፃሉ፡፡

“ስደተኞቹ የተለያዩ ችግሮች ስለሚያጋጥሙዋቸው የምክር አገልግሎትም እንሰጣቸዋለን” ይላሉ አገልጋዩ፡፡

የዓለም የስደተኞችን ቀንን በማስመክለት ገ/ሚካኤል ገ/መድህን ከኤርትራዊው የኃይማኖት አገልጋይ ጋር ያደረገው ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ተከታተሉ።

XS
SM
MD
LG