በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ለመንግሥታት ደብዳቤ ፃፉ


የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ሀገራቸው ላይ ተፈጽሟል ላሉት በደል በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ያላቸውን ተፅዕኖ በመጠቀም ካሣ እንዲያስከፍሉ ለብዙ መንግሥታት መሪዎች ዛሬ መልዕክት ልከዋል፡፡

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ሀገራቸው ላይ ተፈጽሟል ላሉት በደል በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ያላቸውን ተፅዕኖ በመጠቀም ካሣ እንዲያስከፍሉ ለብዙ መንግሥታት መሪዎች ዛሬ መልዕክት ልከዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሣያስ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት፣ የሀገሮችን ሠላምና ፀጥታ በማስከበር ለዓለም ድኅንነት የመሥራት ቀዳሚ ኃላፊነትና ሕጋዊ ግዴታም እንዳለበት በመልክታቸው አስምረውበታል፡፡

የፕሬዚዳንቱ ስሞታ እአአ ከግንቦት 1998 እስከ 2000 በሀገራቸውና በኢትዮጵያ መካከል የተካሄደውንና ከፍተኛ ሕይወትና ንብረት ያወደመውን የድንበር ጦርነት የተመለከተ ነው፡፡

በቅኝ አገዛዝ ዘመን የነበረው ድንበር ግልፅ ሰለነበር፣ “የድንበር ይግባኛ ውዝግቡ” ከተንኮል የመነጨ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ኢሣያስ ሆኖም ዋሺንግተን በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትዋ አማክይነት፣ የአፍሪካ ቀንድን ለመቆጣጠር ጥልቅ የታሪክ ትስስርና እስትራቴጂያዊ አንድነት ባለቸው ሀገሮች መካከል ቅራኔ ፈጥራለች ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ሕጋዊ ኃላፊነቱን በመወጣት፣ ወራሪዎችን ከመሬታቸው የማስለቀቅ፤ አለአግባብ ኤርትራ ላይ ተጣለ ያሉትን ዕቀባ የማንሳትና ኤርትራ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት የማስቆም ግዴታ አለበት ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳል በርካታ የሰብዓዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች ሰለ ኤርትራ ሰብዓዊ መብቶች ዘገባ የሚያቀርብ የመንግሥቱ ድርጀት ልዩ ተጠሪ ኃላፊነት እንዲታደስ ጥሪ አድርገዋል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሺናል እና ሁዩማን ራይትስ ዋችን የጠቀለሉ ሃያ ሰባት ዓለምቀፍና የኤርትራ ሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች፣ ለ35ኛው ዓለምቀፍ የሰብዓዊ መብት ጉባዔ በፃፉት መልዕክት፣ ኤርትራ ሰቆቃ፣ ባርነት፣ አስገድዶ መሰወር እና ሌሎች መሠረታዊ የሆኑ የሰው ልጆች መብት አሁንም የሚጣስበት ሀገር ሰለሆነች፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪ ኃላፊነት እንዲታደስ ጠይቀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ለመንግሥታት ደብዳቤ ፃፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:00 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG