በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ስለሂዩማን ራይትስ ዋች ክሥና ስለኤርትራ ሰብዓዊ መብቶች ከአምባሣደር ግርማ አስመሮም ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

ስለሂዩማን ራይትስ ዋች ክሥና ስለኤርትራ ሰብዓዊ መብቶች ከአምባሣደር ግርማ አስመሮም ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ


አምባሣደር ግርማ አስመሮም - በአፍሪካ ሕብረትና በመንግሥታቱ ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን የኤርትራ አምባሣደር
አምባሣደር ግርማ አስመሮም - በአፍሪካ ሕብረትና በመንግሥታቱ ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን የኤርትራ አምባሣደር

የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት ተቀድዶ መጣል ያለበት ሠነድ ነው ሲሉ በአፍሪካ ሕብረትና በመንግሥታቱ ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮም ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡





ቀጥተኛ መገናኛ

አምባሣደር ግርማ አስመሮም ኤርትራ ውስጥ የግዳጅ ሥራ የለም ሲሉ ባስተባበሉበት ቃለምልልስ የሃገራቸው ብሔራዊ አገልግሎት መርኃግብር ዋና ዋና ዓላማዎች በዘጠኙ የኤርትራ ብሔሮች መካከል የቆየውን ፍቅርና መተሳሰብ ይበልጥ ማጠናከር፣ በመራራ ትግል ያገኙትን የሃገራቸውን ነፃነትና ሉዓላዊነት ማስከበር፣ ዕድሜው ከ15 ዓመት በላይ የሆነ በምንም ሙያ ላይ ያለ ማንም ዜጋ ጉልበቱንና ችሎታውን ሳይቆጥብ ለሃገሩና ለሕዝቡ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያደርገውን አስተዋፅዖ በተደራጀ መልኩ ማካሄድ ናቸው - ብለዋል፡፡

እነዚህ ለብሔራዊ አገልግሎት የሚወጡ ዜጎች በልማትም ይሁን በማንኛቸውም ሥራ ላይ እንደሚሠማሪ አምባሣደር ግርማ አልሸሸጉም፡፡
የሚሠሩትም፣ መብቶቻቸውም ሆነ የሚከፈላቸው የኪስ ገንዘብ እኩል መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዋች ላወጣው ሪፖርት ክብር እንደሌላቸው የገለፁት አምባሣደር ግርማ አስመሮም መግለጫውን “ሆን ተብሎ የሚካሄድ ተንኮል” ነው ብለውታል፡፡

ቃለ-ምልልሱን ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG