በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ ተቃዋሚዎች ሠልፍ በዋሽንግተን ዲሲ


የኤርትራዊያንና ትውልድ ኤርትራ የኤርትራን መንግሥት ተቃውመው ግንቦት 19 ቀን 2003 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በተሠለፉበት ወቅት
የኤርትራዊያንና ትውልድ ኤርትራ የኤርትራን መንግሥት ተቃውመው ግንቦት 19 ቀን 2003 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በተሠለፉበት ወቅት

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ኤርትራዊያንና ትውልድ ኤርትራ የኤርትራን መንግሥት በመቃወም ዛሬ ሰላማዊ ሠልፍ አካሂደዋል፡፡

ሠልፈኞቹ “በኤርትራ የዜጎች መብቶች እየተጣሱ ነው፤ ፕሬዚዳንቱ ሥልጣን መልቀቅ አለባቸው” የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡

“አምባገነን መወገድ አለበት፤ በቃ በቃ፤” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮችን እያሰሙ ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ደጅ ተነስተው ወደዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ተጉዘዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትም የሠልፋቸውን ዓላማ የያዘና የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በኤርትራ መንግሥት ላይ ጫናውን እንዲያበረታ፣ ለኤርትራዊያን ስደተኞችም ትኩረት እንዲሰጥ የሚጠይቅ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG