በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ ሃያኛ የነፃነት በዓሏን አከበረች


ኤርትራ
ኤርትራ

“ካለፉት 15 ዓታት ወዲህ የነበረው ፀረ-ውጥን ጨዋታ…” ያሉት ክስተት “ፀረ-ሉአላዊቷ ሃገር ግንባታ” ነበር ሲሉ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ አስታወቁ፡፡




የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:20 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:35 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:15:10 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

“ካለፉት 15 ዓታት ወዲህ የነበረው ፀረ-ውጥን ጨዋታ…” ያሉት ክስተት “ፀረ-ሉአላዊቷ ሃገር ግንባታ” ነበር ሲሉ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት ለኤርትራ ሃያኛ ዓመት የነፃነት በዓል ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

“ሁኔታው አቅም እንዳናጎለብትና እንዳናበራክት የሚያስተጓጉልና ቀጣይ የሆነ እፎይታ የማናገኝበት ሁኔታ እንዲፈጠር በማድረግ በታጋችነት እንዳንያዝ የሚያደርግ ተግባር እንደነበር በጊዜው ለይተን ለመረዴት አላስቸገረንም” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

የኤርትራው ፕሬዚዳንት አክለውም “እኛ ግን የሉአላዊነት ክብራችን ሳይዛነፍ ለሁሉም የሃገር ግንባታ ዘርፍ ቅድሚያ የመስጠት ጥረት በማድረግ ላይ ተጠምደን ቆይተናል” ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራን ነፃነት ሃያኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የድጋፍና የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡

ሁለቱንም የተከታተለችው የትግርኛ ዝግጅት ክፍል ባልደረባችን ምንያ አፈወርቂ ነች፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቪኦኤ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉ ሁለት ምሁራን የኤርትራን ሁኔታ በየግላቸው ገምግመዋል፡፡

ስለ ሃያ ዓመታቱ የነፃነት ጊዜ ሃሣባቸውን የሰጡት ዶክተር በርሀ ሃብተጊዮርጊስና አቶ ረዘነ ሃብተ ናቸው፡፡

ዶክተር በርሀ ኃብተጊዮርጊስ በዩናይትድ ስቴትስ ኒው ጀርሲ ግዛት ሮዋን ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ ማርኬቲንግ ምርምር ክፍል ፕሮፌሰር ናቸው።

ኢትዮጵያ በነበሩበት ጊዜ ደግሞ የሀገሪቱ የንግድ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ሆነው እንደሰሩና በትምባሆ ሞኖፖል ዋና ሥራ አስኪያጅነትም እንዳገለገሉ ገልፀውልናል።

በፖለቲካል ሳይንስና በቢዝነስ አስተዳደር ማስተርስ ዲግሪ ያላቸው አቶ ረዘነ ኃብተ ደግሞ የዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ ሲሆኑ General Accountability (ጠቅላላ ተጠያቂነት) በተባለ የፌደራል መሥያ ቤት ውስጥ ይሠራሉ።

ፕሮፌሰር በርሀንና አቶ ረዘነን ያነጋገረችው አዳነች ፍሰሀየ ነች፡፡

ሁሉንም ዘገባዎች ከተያያዙት የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG