በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቶ ገብሩ አስራት የኢህአዲግ መግለጫ ለጥያቄዎች መልስ አልሰጠም አሉ


የመድረክ እና የአረና ትግራይ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚተ አባል አቶ ገብሩ አስራት
የመድረክ እና የአረና ትግራይ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚተ አባል አቶ ገብሩ አስራት

የኢህአዲግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰሞኑን ያወጣው መግለጫ እና ያስተላለፈው ውሳኔ በሀገሪቱ ያለውን ችግር ጠባብ በሆነ እና በተለመደ ሁኔታ የተመለከተ ነው ሲሉ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ተናገሩ።

የመድረክ እና የአረና ትግራይ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚተ አባል አቶ ገብሩ አስራት እንዳሉት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መግለጫ በአገሪቱ ባሉ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች የተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ አልሰጠም።

የመንግሥት ስልጣን ለግል መጠቀምያነት መዋሉ የችግሮቹ መንስኤ እንደሆነ እርምጃም እንደሚወስድ የኢህአዲግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰሞኑን ማስታወቁ ይታወሳል።

የገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰሞኑን መግለጫ ያወጣው ከነሃሴ 10-15 ካካሄደው መደበኛ ስብሰባ በኃላ ነው።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

አቶ ገብሩ አስራት የኢህአዲግ መግለጫ ለጥያቄዎች መልስ አልሰጠም አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:45 0:00

XS
SM
MD
LG