በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መተካካት በተቃዋሚዎች ዕይታ


ባሕርዳር
ባሕርዳር

ኢሕአዴግ በያዘው ዕቅድ መሠረት በ2007 ዓ.ም መጨረሻ ወይም በ2008 ዓ.ም መጀመሪያ ነባር ታጋዮች የሚባሉት ሁሉ በሌሎች እንደሚተኩ ይጠበቃል፡፡please wait

No media source currently available

0:00 0:08:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

“መተካካት ሃገራዊ ፋይዳ የሚኖረው ፓርቲዎች ሲተካኩና ኢህአዴግ በተቃዋሚ ሲተካ እንጂ በግለሰቦች መተካካት አይደለም። ኢህአዴግ ግን ለዚህ ዓይነቱ መተካካት ዝግጁ አይደለም” ይላሉ ተቃዋሚዎች።

በኢሕአዴግ መተካካትም ትኩረት የሚሰጠው ብቃትና አገርን የመምራት ችሎታና ብስለት ሳይሆን ለፓርቲ ታማኝነት ነው ይላሉ።

በሦስት ዙር የሚፈፀም የአመራር መተካካት እየተገበረ መሆኑን የሚገልፀው ገዥው ኢሕአዴግ ባሕርዳር ላይ እያካሄደ ባለው ጉባዔው ላይም ይህንኑ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

በተናጠል የተካሄዱ የአራቱ የአሕአዴግ አባል ድርጅቶች ጉባዔዎችም ከገዥው ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት የወጡና በሌሎች የተተኩ ባለሥልጣናትን ማንነት አሣውቀዋል፡፡

አራቱ ፓርቲዎች የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሚሆኑ ዘጠኝ ዘጠኝ ሰዎችን መርጠው ወደ ባሕርዳር ልከዋል፡፡

በዘንድሮው ጉባዔ ኢሕአዴግ ስምንት ነባር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባላቱን ያሰናበተ ሲሆን በያዘው ዕቅድ መሠረትም በ2007 ዓ.ም መጨረሻ ወይም በ2008 ዓ.ም መጀመሪያ ነባር ታጋዮች የሚባሉት ሁሉ በሌሎች እንደሚተኩ ይጠበቃል፡፡

የእስክንድር ፍሬው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል።
XS
SM
MD
LG