በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው የምስረታ ጉባኤ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧቸዋል፡፡

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የምስረታ ጉባኤ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧቸዋል፡፡ አቶ አባዱላ ገመዳን ደግሞ በዋና አፈ ጉባኤነት በድጋሚ መርጧቸዋል። የመመስረቻ ጉባኤው ወይዘሮ ሽታዬ ምናለን በምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤነት መርጧል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባካሄደዉ ጉባኤ አቶ ያለዉ አባተን በአፈ ጉባኤነት እንዲሁም አቶ መሐመድ ረሽድ መርጧል፡፡ ምርጫው በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ሰብሳቢነት ነው የተከናወነው። ተመራጮቹ ምክር ቤቱ የሰጣቸው ሀላፊነት በቅንነት ለመወጣት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

ይህ እስክንድር ፍሬው አቀናብሮ የላከው ፎቶ መድብል ነው።


XS
SM
MD
LG