አዲስ አበባ —
የኢህሃዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ እየተካሄደ ባለው ለውጥና በሕግ የበላይነት መከበር ላይ እየተወያዩ መሆኑ ተገለጠ፡፡
ከ36ቱ የኢህሃዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አንዱና በግንባሩ ጽ/ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማኅበራትና የአጋር ድርጅቶች አስተባባሪ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ እንዳስረዱት በተጠቀሱት ርዕሶችና በተያዙ ጉዳዮች ላይ ነፃና ግልፅ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
-
እስክንድር ፍሬው