በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢሕአዴግና የአባል ድርጅቶቹ ጉባዔዎች


ኢሕአዴግ
ኢሕአዴግ

አባላቱንና ተጋባዦችን ጨምሮ 2500 ተሣታፊዎች ይገኙበታል የተባለው የኢሕአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ከመጋቢት 14 / 2005 ዓ.ም ጀምሮ በባሕርዳር ከተማ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አባላቱንና ተጋባዦችን ጨምሮ 2500 ተሣታፊዎች ይገኙበታል የተባለው የኢሕአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ከመጋቢት 14 / 2005 ዓ.ም ጀምሮ በባሕርዳር ከተማ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

ኢሕአዴግ የጀመረው የመተካካት ሂደት በባሕርዳሩም ጉባዔ እንደሚቀጥል አዘጋጆቹ መግለፃቸው ይታወሣል፡፡

ከዚያ ቀደም ብሎ ሰሞኑን የተካሄዱት የአባል ድርጅቶች የተናጠል ጉባዔዎችም በባሕርዳሩ ስብሰባ ሊኖሩ ስለሚችሉ የአመራር ለውጦች መረጃ መስጠት ጀምረዋል፡፡

የኢሕአዴግን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚመሠርቱት የአራቱ አባል ድርጅቶች፤ ማለትም የኦሕዴድ፣ የሕወሓት፣ የደኢሕዴን እና የብአዴን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው የሚመረጡት ከእያንዳንዳቸው የሚውጣጡ ዘጠኝ ዘጠኝ ሰዎች ናቸው፡፡

ኦሕዴድ ባደረገው ድርጅታዊ ስብሰባው አራት ነባር ባለሥልጣናትን ከሥራ አስፈፃሚ ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ ከማዕከላዊ ኮሚቴው ደግሞ ሌሎች ሦስት ሰዎችን ወደሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አስገብቷል፡፡

ብአዴን ደግሞ ቀደም ሲል ተሰናብተው የነበሩትን አቶ አዲሱ ለገሠን ወደ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መልሷል፡፡

ደኢሕዴን ደግሞ ሁለት መሪዎቹን ከሥራ አስፈፃሚው ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ አዛውሮ በሁለት አዳዲስ አባላት ተክቷል፡፡

ሕወሓትም የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባላት የነበሩ አንዳንድ ነባር ባለሥልጣናትን በአዳዲሶች ተክቷል፡፡

ለአራት ቀናት የዘለቁት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ጉባዔዎች የየድርጅቱን ማዕከላዊና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎችን አባላት በመምረጥ ተጠናቅቀዋል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፎቶግራፎች በትልቁ የተለጠፉባቸው የባህር ዳር፣ የሐዋሳ፣ የመቀሌና የአዳማ ጉባዔዎች የአቶ መለስን ፖሊሲዎችና ስልቶችን ለማስፈፀም ቃል ገብተዋል።

ዝርዝሩን ከዘገባዎቹ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG