በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የግንቦት 20 ክብረ-በዓል የመልካም ምኞት መግለጫ

የደርግ መንግሥት የወደቀበትና ኢሐዴግ ወደ ሥልጣን የመጣበት የግንቦት 20 በዓል 27ኛ ዓመት ዛሬ ተከብሯል። የግንቦት 20ን ክብረ-በዓል በተመለከተም፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል፣ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።

የደርግ መንግሥት የወደቀበትና ኢሐዴግ ወደ ሥልጣን የመጣበት የግንቦት 20 በዓል 27ኛ ዓመት ዛሬ ተከብሯል። የግንቦት 20ን ክብረ-በዓል በተመለከተም፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል፣ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።

“በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕና በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ስም፣ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የመልካም ምኞት መግለጫዬን አስተላልፋለሁ“ በማለት፣ ውጩ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ ናቸው መልዕክቱን ያስተላለፉት።

ዩናይትድ ስቴትስና ኢትዮጵያ የቆየ ወዳጅነትና የጋራ ትብብር ያላቸው አገሮች መሆናቸውን ያመለከተው ይኸው መግለጫ፣ እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ኗሪ በሆኑና ጠቃሚ አስተዋፅዖ በሚያደርጉ ኢትዮ-አሜሪካውያን፣ የሁለቱ አገሮች ወዳጅነት የፀና መሠረት እንዳለውም ጠቅሷል።

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ግልፅነትን እንደጀመሩና የኢኮኖሚ ድል እንዳስመዘገቡም የሚናገረው ይኸው የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሙሉ የዩናይትድ ስቴትስ ትብብር እንዳላቸውም ያረጋግጣል።

“መልካም በዓል ዩናይትድ ስቴትስ ለጋራ ወዳጅነታችን ያላትን ቁርጠኛነት ታረጋግጣለች“ በማለትም መልዕክቱን ይደመድማል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG