በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢሕአዴግ ዘጠነኛው ጉባዔ ፍፃሜ


ባሕርዳር - “ዋይት ሃውስ” - የአማራ ክልል መስተዳድር ሕንፃ
ባሕርዳር - “ዋይት ሃውስ” - የአማራ ክልል መስተዳድር ሕንፃ

“ታላቁ መሪ” እየተባሉ የተወደሱት መለስ ዜናዊ ካረፉ በኋላ ኢሕአዴግ ያደረገውን የአመራር ለውጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝን ሊቀመንበሩ አድርጎ በመምረጥ አጠናቅቋል፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ባሕርዳር
ባሕርዳር

“ታላቁ መሪ” እየተባሉ የተወደሱት መለስ ዜናዊ ካረፉ በኋላ ኢሕአዴግ ያደረገውን የአመራር ለውጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝን ሊቀመንበሩ አድርጎ በመምረጥ አጠናቅቋል፡፡
ኢሕአዴግ
ኢሕአዴግ

ይህ የግንባሩ ጉባዔ ካከናወናቸው ሌሎች ተግባራት መካከል አዳዲስ ሰዎችን ወደአመራሩ ማምጣትን ያካተተም እንደነበረ ታውቋል፡፡
ባሕርዳር
ባሕርዳር

የውሣኔ ሰጭነት ቦታቸውን ከለቀቁት መካከል ስሞቻቸው ገንነው የሚታወቁ የግንባሩ ቁልፍ አካል ነው የሚባለው የህወሓት ነባር ሰዎች ይገኙባቸዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባላት የነበሩት አቶ ፀጋይ በርሀ እና አባዲ ዘሞ፣ እንዲሁም የማዕከላዊ ኮሚቴው አባላት የነበሩት ስዩም መስፍን፣ አርከበ ዑቕባይ፣ ብርሃነ ገብረክርስቶስ እና ዘርዐይ አስገዶም ይገኙባቸዋል፡፡
ባሕርዳር
ባሕርዳር

በሌላ በኩል ደግሞ ላለፉት የፓርቲው መሪ ለአቶ መለስ ዜናዊ የተዘጋጀው ዝክረ-መወድስ ብዙ የጉባዔው ልዑካንን አለማስደሰቱን ፎርቹን የሚባለው የንግድና ምጣኔኃብት ርዕሰ-ጉዳዮች ጋዜጣ ፅፏል፡፡

ዝክረ-መወድሱ ቀደም ሲል መቐለ ላይ በተካሄደው የህወሓት ጉባዔ ላይ የቀረበ ሲሆን በባሕርዳሩ የኢሕአዴግ ጉባዔ ፍፃሜ ላይም በድጋሚ ተሰምቷል፡፡
ባሕርዳር
ባሕርዳር

ደስተኛ አይደሉም ከተባሉት መካከል የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን አንዷ ሲሆኑ ዝክረ-መወድሱ ከአቶ መለስ የሕይወት ጉዞ ብዙ ቁምነገሮችን የዘለለና ያልተሟላ ነው ሲሉ መደመጣቸው ተነግሯል፡፡

በቃሉ ውስጥ አልተጠቀሱም ብለው ወ/ሮ አዜብ ቅሬታቸውን ከገለፁባቸው ሥራዎቻቸው መካከል አቶ መለስ የድርጅታቸው ልሣን የነበረው አዲስ ራዕይ ዋና አዘጋጅ እንደነበሩ አለመታወሱ እንደሚገኝበት ታውቋል፡፡

የዝክረ-መወድሱ ቃል የተነበበው በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ነው፡፡
ባሕርዳር
ባሕርዳር

በባሕርዳሩ ኢሕአዴግ ጉባዔ ላይ ከተስተዋሉ ሌሎች ጉልህ ጉዳዮች መካከል የሌሎች ሃገሮች በርካታ የሶሻሊስትና የኮምዩኒስት ፓርቲዎች ልዑካን በታዛቢ እንግድነት መገኘታቸው ይጠቀሣል፡፡
ባሕርዳር
ባሕርዳር

ስፋት ያለውና ከፍተኛ ቦታ የተሰጠው የልዑካን ቡድን የቻይና ኮምዩኒስት ፓርቲ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

የቻይና ኮምዩኒስት ፓርቲ በኢሕአዴግ ዘንድ እንደአርአያ እንደሚታይ ይታወቃል፡፡

ባሕርዳር
ባሕርዳር
XS
SM
MD
LG