No media source currently available
ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ አሁን ለኮሮናቫይረስ መጋለጡ የተረጋገጠ ሰው የለም። የመከላከልና የክትትል ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲል የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። በኢንስቲትዩቱ ከዚህ ቀደም ተመርምረው ከቫይረሱ ነጻ ከሆኑት ናሙናዎች ውስጥ 45 በመቶው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልከው ዳግም መመርመራቸው እና ውጤቱ ተመሳሳይ መሆኑ መረጋገጡንም ጨምሮ አመልክቷል።