በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቅዱስ ሲኖዶስን የገጠመው ፈተና፣ የመጣበት መንገድ እና ዛሬ የተደረሰበት


ቅዱስ ሲኖዶስን የገጠመው ፈተና፣ የመጣበት መንገድ እና ዛሬ የተደረሰበት
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:32 0:00

መንግሥት የቤተክርስቲያንን አቋም ሙሉ በሙሉ መቀበሉን በመግለጽ፣ ለነገ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለሌላ ጊዜ ማራዘሙን ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ።

መንግሥት የቤተክርስቲያንን ጥሪ ተቀብሎ የውይይት መድረክ በማዘጋጀት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንደሚፈጸም ማረጋገጡንም ሲኖዶስ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በቤተክርስቲያኗ የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ የሰው ህይወት አስከማጥፋት የደረሰ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላት ለህግ እንዲቀርቡም ሥምምነት መደረሱን ሲኖዶሱ ገልጿል፡፡ ከመንግሥት በኩል ግን ስለተደረገው ውይይትም ይሁን ስለተደረሰው ሥምምነት እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ሕገወጥ ነው የሚለው እና ራሱን “የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ” በማለት የሚጠራው አካልም በተመሳሳይ ለየካቲት 5 የጠራውን ሰልፍ ለሌላ ጊዜ ማራዘሙን ትናንት መግለጹ ይታወቃል፡፡

የዛሬውን መረጃ ጨምሮ፣ የቤተክርስቲያኗ ችግር ከየት ተነስቶ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ኬኔዲ አባተ በተከታዩ ዘገበ ያስቃኘናል፡፡

XS
SM
MD
LG