በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት ገብቶበታል ከተባለው የኃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንዲታቀብ ተጠየቀ


የኢትዮጵያ መንግሥት ገብቶበታል ከተባለው የኃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንዲታቀብ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:40 0:00

ትላንት እሁድ ጥር 28፤ 2015 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሪ አባቶችና ምዕመናን ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ፤ “መንግሥት ቤተክርስቲያኒቷን ከሚከፋፍል አካሄድ ይታቀብ” ሲሉ ጠይቀዋል።

ቁጥራቸው የበዛ ኢትዮጵያውያን እና ትወልደ ኢትዮጵያ በተሳተፉት በዚሁ ሰልፍ ላይ፤ ጉዳዩ ተካሮ ደም አፋሳሽ እንዳይሆን ከወዲሁ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት መፍትሔ እንዲያፈላልጉ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ትላንት በጹሑፍ ባወጣው መግለጫ "በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በውስጣዊ አሠራር መፈታት እንዳለበት መንግሥት ያምናል" ብሏል።

ችግሩን ለማባባስ፣ በሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር ብሎም ሀገርን ወደ ፈተና ለማስገባት ይጥራሉ ባላቸው አካላት ላይ መንግሥት ‘የህግ ማስከበር’ ያለውን ሥራ እንደሚሠራ አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG