በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የቀብር ሥነ ስርዓት

የህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ የቀብር ሥነ ስርዓት

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሐምሌ 22 ቀን 2010 ዓ.ም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤቴክርስትያን ተፈጽሟል።
መስከረም 3/1957 ዓ.ም በጎንደር ማክሰኝት የተወለዱት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ የመጀመርያና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ቅዳሜ ገበያና እንፍራንስ ትምህርት ቤቶች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በወልዲያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቀዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1989 ዓ.ም. በምሕንድስና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ፣ ኮተቤ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማሠልጠኛ ተቋም ከ1990 እስከ 1991 ዓ.ም ድረስ በመምህርነት አገልግለዋል፡፡
በ1992 ዓ.ም ለአንድ ዓመት በኮርፖሬሽኑ የኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ውስጥ ከሠሩ በኋላ፣ ከ1993 እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ በተገነባው ግልገል ጊቤ አንድ የኃይል ማመንጫ አስተባባሪ መሐንዲስ ከ1998 እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ የተገነባው ግልገል ጊቤ ሁለት የኃይል ማመንጫ ሥራ አስኪያጅ ሆነው አሠርተዋል፡፡
ከመጋቢት 2003 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ደግሞ ኢትዮጵያ ሕዝብ ምልክት ይሆናል በተባለው የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው እያሠሩ ነበር፡፡ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ባለትዳርና የሁለት ወንዶችና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበሩ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG