በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጊምቦ ጎኦታ ከምርጫ ጋር በተያያዘ አንድ ሰው ተገደለ፤ ምርጫው ተላለፈ


ቦንጋ
ቦንጋ

በደቡብ ኢትዮጵያ ከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ ጊምቦ ጎአታ የምርጫ ክልል ከምርጫ ጋር በተያያዘ በተነሣ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉና ብዙዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል፡፡ ምርጫው ላልተወሰ ጊዜ ተላልፏል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:14:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በደቡብ ኢትዮጵያ ከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ አካባቢ ማለት ጊምቦ ጎአታ የምርጫ ክልል ለፊታችን ዕሁድ - ግንቦት 16/2007 ዓ.ም ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የድምፅ መስጫ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን የዞኑ የምርጫ አስተባባሪ በተለይ ለአሜሪካ ድምዕ ራድዮ ተናግረዋል።

በዚህ ተሰናባች የምርጫ ክልል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛው የግል የፓርላማ አባል ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የሚወዳደሩ ሲሆን በገጠር አካባቢዎች የምረጡኝ ዘመቻዎቸው ያካሄዷቸው ቅስቀሣዎች በፀጥታ ኃይሎችና በአካባቢው መስተዳድር ተባብረው ፈፀሙት በሚሉት ድብደባ አንድ ሰው ተገድሏል፡፡

ሌሎች ከአሥር በላይ መቁሰላቸው ታውቋል።

በዚህም ምክንያት ካሁን በፊት ያሸነፉት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እና ደጋፊዎቻቸው የምርጫ ዘመቻቸውን አቋርጠዋል።

በጊምቦ ጎአታ የምርጫ ክልል ቦንጋ አካባቢ የዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የምርጫ ምልክት ላም ስትሆን ገዥው ፓርቲ ደኢህዴግ/ኢህአዴግ ዕጩ ዶክተር መብራቱ ገብረማርያም በንብ ምልክት ተፋጠዋል።

ሰማያዊ ፓርቲ፥ ቅንጂት፥ ኢዴፓ፥ መኢአድ፤ መድረክና ሪፓ ፓርቲዎች በምርጫው በመሣተፍ ዝግጅት ላይ የነበሩ ሲሆን የምርጫው ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ተቃውመዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG