በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥርጣሬ እንዲወገድ ኤል-ሲሲ ጠየቁ


አብዱልፋታህ ኤል-ሲሲ - የግብፅ ፕሬዚዳንት /ፎቶ ፋይል/
አብዱልፋታህ ኤል-ሲሲ - የግብፅ ፕሬዚዳንት /ፎቶ ፋይል/

ስምምነቱን እንደሚደግፉ የመድረክ ሊቀመንበር አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያን ጥቅሞች እንዳይጎዳ ጥንቃሴ እንዲደረግ አሳሰቡ፡፡

የኢትዮጵያ ፓርላማ
የኢትዮጵያ ፓርላማ

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኢትዮጵያና ግብፅ ጥርጣሬን አስወግደው መተማመንን ለማጠናከር መሥራት እንዳለባቸው የግብፅ ፕሬዚዳንት አሳሰቡ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉትን የሦስት ቀናት ይፋ ጉብኝት ዛሬ የፈፀሙት ፕሬዚዳንት አብዱልፋታህ ኤልሲሲ ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ጥምር ስብሰባ ዛሬ ባደረጉት ንግግር የፖለቲካ ስምምነቱን ለመተግበር መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

የግብፁ ፕሬዚዳንት ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ጋር ተወያይተዋል፡፡

/ለዝርዝሩ ዘገባውን የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

በሌላ በኩል ደግሞ ስምምነቱን በፀጋ እንደሚቀበሉት የተቃዋሚው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት ዴሞክራሲያዊ መድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አስታውቀዋል፡፡

በየነ ጴጥሮስ - ፕሮፌሰር /የመድረክ ሊቀመንበር/
በየነ ጴጥሮስ - ፕሮፌሰር /የመድረክ ሊቀመንበር/

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያን ጥቅሞች አሳልፎ እንዳይሰጥ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ፕሮፌሰር በየነ አክለውም “… ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ከዚህ በፊትም ባደረጋቸው ጎረቤትዊና ዓለምአቀፋዊ ድርድሮች ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብና ሃገር መብት በማስከበር በኩል ያለው ያለፈ ታሪክ ይህንን ያህል የሚያስመካ አይደለም… ለዚህም የአልጀርሱን ስምምነት መጥቀስ እችላለሁ … የአሰብ የባሕር በር ባለቤትነት ጉዳይም የኢትዮጵያ ጥቅም የተከበረበት አይደለም የሚል አቋም ነው የያዝነው…” ብለዋል፡፡

/ለሙሉው ቃለምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG