ኢትዮጵያ፣ በሰላም ዕጦት እና በተፈናቃዮች መብዛት እየተፈተነች በምትገኝበት በአሁኑ ወቅት፣ ሕዝበ ሙስሊሙ፣ በቅዱሱ ወርኀ ረመዳን ያሳየውን በጎነት እና ለጋስነት፣ ከዒዱም በኋላ ሳያቋርጥ አጠናክሮ እንዲቀጥልበት ተጠየቀ፡፡
ለሕዝበ ሙስሊሙ፣ ለተቸገሩት መድረስ እና ደካሞችን ማገዝ ሃይማኖታዊ ግዴታው ቢሆንም፣ ቀጣይነቱ ለዛሬዪቱ ኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በሌሎችም ወራት እንዲቀጥል፣ 1ሺሕ444ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል፣ በብሔራዊ ደረጃ በተከበረበት የዐዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ የዒድ ሶላት ሥነ ሥርዐት ላይ ያነጋገርናቸው፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ሼሪአ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሼሕ ሙባረክ ሼሕ መሐመድ አወል እና ሌሎችም ታዳሚዎች ተማፅነዋል፡፡