በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመብቶች ኮሚሽኑ በትግራይ ተፈናቃዮች ላይ


የመብቶች ኮሚሽኑ በትግራይ ተፈናቃዮች ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:26 0:00

በአማራ ክልል ወሎ አካባቢ በጃራና ጃሬ ካምፖች ውስጥ ባለው የትግራይ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ በአፋር ክልል በሰመራና አጋቲና ካምፖች ውስጥም ላለፉት ስምንት ወራት ተይዘው የቆዩ የትግራይ ተወላጆችን ወደየመኖሪያ አካባቢያቸው መመለስ መጀመሩንም አድንቋል።

በኮሚሽኑ የአፋር ክልል የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ግርማይ የኮሚሽኑን መግለጫ አስመልክተው ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ በሰዎቹ አያያዝ ላይ የሚደረገው ክትትል እንደቀጠለ መሆኑን፣ የተመለሱት ቁጥርም በመጨረሻው የክትትል ሪፖርት እንደሚገለፅ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን 9 ሺህ እንደሚሆኑ የገመታቸው፤ የአፋር ክልል ደግሞ 7 ሺህ 800 ናቸው የሚላቸው የትግራይ ተወላጆች መመለስ የጀመሩት በዚህ ሣምንት ነው።

XS
SM
MD
LG