በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢሰመኮ የዐማራ ክልል ውጥረት በውይይት እንዲፈታ አሳሰበ


ኢሰመኮ የዐማራ ክልል ውጥረት በውይይት እንዲፈታ አሳሰበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:49 0:00

በዐማራ ክልል፣ “የሕግ ማስከበር” በሚል በፌዴራሉ መንግሥት እየተወሰደ ያለው ወታደራዊ ርምጃ፣ በጣም አሳሳቢ እንደኾነና ችግሩ በውይይት እንዲፈታ፣ ኢሰመኮ የተወካዮች ምክር ቤትን አሳሰበ፡፡

በዐማራ ክልል ከሚደረገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ በተጨማሪ፣ የዘፈቀደ እስር እና ተገቢ ያልኾነ አያያዝ፣ ተመጣጣኝ ያልኾነ የኃይል አጠቃቀም፣ በብዙኃን መገናኛ እና በተቃዋሚዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት፣ ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀሰ መብት ላይ የተጣለ የዘፈቀደ ገደብ፣ ሕጋዊ ሒደትን ያልተከተለ የቤቶች ፈረሳ እና ሌሎችም የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች እጅግ አሳሳቢ ኾነው መቀጠላቸውን፣ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የ2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ ክንውን ሪፖርቱን፣ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ፣ ዋና ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣ “በጣም አሳሳቢ ኾነው ቀጥለዋል፤” ያሏቸውን ልዩ ልዩ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮችን አንሥተዋል፡፡

ከእነዚኽም መካከል፣ በዐማራ ክልል፣ በሰላማውያን ሰዎች ላይ፣ “እስከ ሞት የደረሰ የሰብአዊ መብቶችን ጥሰት ያስከተለ” ያሉት ወታደራዊ ርምጃ እንደሚገኝበት የገለጹት ዶ/ር ዳንኤል፣ ችግሩ በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት አሳስበዋል፤ ከምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ለተነሡላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

/ሙሉ ዘገባው ከፋይሉ ጋራ ተያይዟል/

XS
SM
MD
LG