የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በጋምቤላ ክልል ከግንቦት 2015 እስከ ጥር 2016 ዓ.ም ድረስ በተከሠቱ ግጭቶች፣ ቢያንስ 138 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ፣ በግጭቱ የንብረት ውድመት እና ዘረፋ መፈጸሙንም በምርመራው ማረጋገጡን ጠቅሷል።
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አቤል አዳነ፣ ስለ መግለጫው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፣ በግጭቱ በጋምቤላ ክልል የሚኖሩ ስደተኞችም እንደተሳተፉ ተናግረዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጠው የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በበኩሉ፣ ባለፈው ዓመት ከግንቦት እስከ ነሓሴ ወራት ድረስ አጋጥሟል ባለው ግጭት፣ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱን አምኖ፣ መጠኑን ግን አልገለጸም፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ዲሴምበር 24, 2024
ምርታቸውን በከፍተኛ ዋጋ የሸጡ የቡና ገበሬዎች
-
ዲሴምበር 24, 2024
አሸብራቂዎቹ የኒው ዮርክ የገና መብራቶች ቱሪስቶችን ከመላው ዓለም እየሳቡ ነው
-
ዲሴምበር 24, 2024
ለዩናይትድ ስቴትስ መገናኛ ብዙኅን የፈተናዎች እና የድሎች ዓመት ሆኖ ያለፈው 2024
-
ዲሴምበር 23, 2024
በ2024 ረዥም ጊዜ የቆዩ አንዳንዶቹ ገዢ ፓርቲዎች ሲቀጥሉ፣ ሌሎች ከባድ ሽንፈት ገጥሟቸዋል
-
ዲሴምበር 23, 2024
የአይቮሪ ኮስት ወንዶች ስለ ስንፈተ-ወሲብ ምን ይላሉ?
-
ዲሴምበር 23, 2024
የማላዊ ጋዜጠኞች ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል እውነትን የማጣራት ክህሎት እየተማሩ ነው