በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል 50 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ኢሠመኮ አስታወቀ


በኦሮሚያ ክልል 50 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ኢሠመኮ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:25 0:00

ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ብቻ ቢያንስ 50 የሚሆኑ ሰዎች ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት በፈረጀውና “ሸኔ” ብሎ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ትናንት አስታውቋል፡፡

ከአዲስ አበባ 380 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በምትገኘው የአኖ ከተማ የተፈጸመው ግድያ በዋናነት ቀድሞውንም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሰዎችን ዒላማ ያደረገ እንደነበር የኮሚሽኑ ሪፖርት አመልክቷል፡፡

የሰለባዎቹን ቤተሰቦች፣ የዓይን እማኞች እና የመንግሥት አካላትን ጠቅሶ የወጣው የኮሚሽኑ ሪፖርት ለጥቃቱ “ሸኔ” ብሎ የጠራውን ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ አድርጓል። የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ድምፅ በዚሁ ጉዳይ በሰጡት ቃል በአካባቢው የሚገኝ ማሰልጠኛ ላይ ጥቃት ከማድረስ ውጪ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት አልሰነዘርም ሲሉ አስተባብለው ነበር።

ሆኖም የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ባለፈው ሳምንት ወደ ስፍራው አቅንቶ ያነጋገራቸው ልጆቻቸው የተገደሉባቸው ወላጆች ግድያው የተፈፀመው “ሸኔ” ብለው በጠሩት ታጣቂዎች መሆኑን ተናግረዋል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG