አዲስ አበባ —
በሰሜን ወሎ ቆቦ እና አካባቢው በህወሓት ኃይሎች በተፈፀመ ጥቃት ከ500 በላይ ሰዎች ስለመገደላቸው መረጃዎች እንደደረሱት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ/ኢሰመጉ/ ገለጸ።
ጳጉሜ 5/2013 ዓ.ም ተፈጸመ በተባለው ጥቃት የእርሻ ሰብልን ጨምሮ የግለሰብ እና የሕዝብ ንብረት መውደሙን እንዲሁም በርካታ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውንም በተመለከተ መረጃዎች እንደረሱት ኢሰመጉ አስታውቋል፡፡
ይሁን እንጂ ህወሓት ከዚህ ቀደም በተለያየ መልኩ በሰጣቸው መግለጫዎች፣ በንጹኃን ላይ ኃይሎቹ ፈጽመዋል የሚባሉ የግድያ እና ሌሎች ኢሰብዓዊ ጥቃቶችን እንደማይቀበል መግለጹ ይታወሳል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡