በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግብፅ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ታወጀ


ትናንት እሁድ ግብፅ ውስጥ በሁለት ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን ቢያንስ አርባ አራት ሰዎች ለገደሉት የቦምብ ጥቃቶች ራሱን "እስላማዊ መንግሥት" ብሎ የሚጠራው ቡድን ኃላፊነት ወሰደ፡፡

ትናንት እሁድ ግብፅ ውስጥ በሁለት ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን ቢያንስ አርባ አራት ሰዎች ለገደሉት የቦምብ ጥቃቶች ራሱን “እስላማዊ መንግሥት” ብሎ የሚጠራው ቡድን ኃላፊነት ወሰደ፡፡

የሆሳዕናን በዓል ቅዳሴ ምዕመናን በታደሙባቸው አብያተ ክርስቲያናት የመጀመሪያው ቦምብ የፈነዳው ከዋና ከተማዋ ከካይሮ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ባለችው ታንታ ከተማ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲሆን ቢያንስ ሃያ ሰባት ሰዎች ገድሎ ሌሎች ብዙዎች ማቁሰሉን የመንግሥቱ ቴሌቭዥን ዘግቧል።

ቦምቡ በዋናው ቤተ መቅደስ ወንበር ሥር ተጠምዶ የነበረ መሆኑን አክለዋል።

ብዙም ሳይቆይ እስክንድሪያ ከተማ ቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል በሩ ላይ ቦምብ ፈንድቶ ቢያንስ አሥራ ሰባት ሰው ገደለ ። የዓይን ምስክሮች እንዳሉት ፖሊሶች አጥፍቶ ጠፊው ወደ ቤተክርስቲያኑ ሊገባ ሲል እንደያዙት ነው በላዩ የለበሰውን ቦምብ ያፈነዳው።

የቦምብ ጥቃቶቹ ከታላላቅ የክርስትና እምነት በዓላት አንዱ በሆነው በሆሳዕና ዕለት የተፈፀሙት ሆን ተብሎ ብዙ ሰው እንዲጎዱ ታልሞ እንደሆን ነው የተገለፀው።

የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፅዕ አቡነ ቴዎድርስ በእስክንድሪያው ካቴድራል የሆሳዕና በዓል ቅዳሴ ሥርዓት ላይ እንደነበሩና በቦምብ ጥቃቱ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸው የመንግሥቱ ቴሌቪዥን ገልጿል።

የግብፁ ፕሬዚደንት አብደልፋታህ ኤል ሲሲ የቦምብ ጥቃቶቹን ተከትሎ ለሦሥት ወራት የሚቆይ አስቸኳይ ጊዜ ዓውጇል።

በግብፅ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ታወጀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:17 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG