ዋሺንግተን ዲሲ —
ጋዜጠኛ አብደል ሃሊም ቋንዲል የሀገሪቱን የፍርድ ሥርዓት ነቅፏል ተብሎ ካች አምና ታህሳስ ወር ላይ የሦስት ዓመታት እስራት ተፈርዶበት እንደነበር የአረብ የግብፁ ሪፖብሊክ ኦፊሴላዊ መጽሄት ትናንት ዘግቧል።
ቋንዲል ከ17 ሌሎች ተከሳሾች ጋር በአንድ ዓይነት ክስ ነበር የተፈረደበት። የሙስሊም ወንድማማችነት ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ ይገኙባቸዋል።
የሙስሊም ወንድምማችነት ድርጅት ተቃዋሚ የሆነው ጋዜጠኛ በሞርሲ ላይ የተፈፀመውን የመንግሥት ግልበጣ ደግፎ ነበር። የ65 ዓመት ዕድሜው ጋዜጠኛ የአልሲሲ መንግሥት ደጋፊ ቢሆንም የመዘዋወር ዕገዳ ተደርጎበት፣ ጋዜጣው እንዳይታተም ታግዷል።
ሆስኒ ሙባረክ ከስድስት ዓመታት በፊት ከሥልጣን ተወግደው አልሲሲ ሥልጣን ላይ ከወጡበት ጊዜ አንስቶ በተቃውሞ ላይ ከባድ ዕርምጃ ወስደዋል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አብዛኞቹ እሳማውያንና አለማውያን አክቲቪስቶችን አስረዋል። ከአብዮቱ በኋላ የተገኘውን ነፃነትንም ገድበዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ