በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ


ሞሐመድ ካመል አምር - የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ሞሐመድ ካመል አምር - የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ባለው የኅዳሴ ግድብ ዙሪያ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ላይ ለመነጋገር በግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐመድ ካመል አምር የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

የኅዳሴ ግድብ ንድፍ
የኅዳሴ ግድብ ንድፍ
አባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ባለው የኅዳሴ ግድብ ዙሪያ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ላይ ለመነጋገር በግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐመድ ካመል አምር የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ማምሻውን ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ የልዑካን ቡድኑ ከኢትዮጵያ አቻው ጋር ነገ ሰኞ፣ ሰኔ 10/2005 ዓ.ም ጠዋት ለውይይት እንደሚቀመጥ ታውቋል፡፡

ለጊዜው ቁጥሩን ባይጠቅሱም የግብፁ ቡድን በርካታ አባላት ያሉት መሆኑን አምባሣደር ዲና አመልክተው ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘው በራሷ በግብፅ ጥያቄ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ኅዳሴ ግድብ በግንባታ ላይ
ኅዳሴ ግድብ በግንባታ ላይ
ሰሞኑን የግብፅ ባለሥልጣናት በግድቡ ግንባታ ላይ እያሰሙ ያሉትን ነቀፌታና ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ ለሕዝባቸው በቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር ያስተላለፉትን ዛቻና ማስፈራሪያ መሰል መልዕክት አስመልክቶ ማብራሪያ ለመጠየቅ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ አበባ የሚገኙትን የግብፅ አምባሣደር ሁለት ጊዜ ጠርቶ ማነጋገሩንም አምባሣደር ዲና አመልክተዋል፡፡
አምባሣደር ዲና ሙፍቲ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
አምባሣደር ዲና ሙፍቲ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

የሰኞው ውይይት ይጠናቀቃል የተባለው ነገ ረፋድ ላይ በሚደረገው ውይይት ሲሆን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር የቡድኑ ጉብኝት የተያዘው ለአንድ ቀን ብቻ መሆኑን የውጭ ጉዳዩ ቃልአቀባይ ገልፀዋል፡፡

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:01:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG