በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአባይ ጉዳይ ንግግሮች እንደሚቀጥሉ የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ጠቆሙ


ሃዘም ኤል-ቤብላዊ - የግብፅ የሽግግር ጠቅላይ ሚኒስትር
ሃዘም ኤል-ቤብላዊ - የግብፅ የሽግግር ጠቅላይ ሚኒስትር

ከኢትዮጵያ ግዙፉ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታና አባይ ወንዝ ጉዳይ የተያያዘው የግብፅና የኢትዮጵያ ድርድር አለመቆሙን ወይም አለመቋረጡን የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ማስታወቃቸው ተዘግቧል፡፡




ኅዳሴ ግድብ ፕሮጀክት
ኅዳሴ ግድብ ፕሮጀክት

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:37 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከኢትዮጵያ ግዙፉ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታና አባይ ወንዝ ጉዳይ የተያያዘው የግብፅና የኢትዮጵያ ድርድር አለመቆሙን ወይም አለመቋረጡን የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ማስታወቃቸው ተዘግቧል፡፡

ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ላይ ባለፉት ቅዳሜና ዕሁድ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ባካሄዱት ስብሳባ ላይ የግብፅ ቡድን ይዞ የቀረበውን “መተማመን ማጎልበቻ መርኅ” የሚል ሰነድ ኢትዮጵያ ሳትቀበል ቀርታለች፡፡
ለምን? በስብሰባውና በቀደሙትም ድርድሮች ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ለቪኦኤ በሰጡት ቃለምልልስ ግብፃዊያኑ “የመተማመኛ ማጎልበቻ መርኅ” ብለው ይዘው የቀረቡት ሰነድ ኢትዮጵያ ከ84 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር የናይል ውኃ የ55.5 ቢሊየኑን ድርሻ ለግብፅ ተጠቃሚነት የሚደነግጉትን የ1929 እና የ1959 ዓ.ም ስምምነቶችን ሃሣብ እንድትቀበል፤ በመረጃ ልውውጥ ላይ በናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ውስጥ የተካተተን አሠራር ተቋሙን ሊጋፋ በሚችል ሁኔታ እንድትስማማ እና ሥራዎቿን እየቀደመች እንድታሣውቅ የሚል “ፍቃድ የመጠየቅ ያህል የሚታይ” ያሉትን ሃሣቦች ያካተተ በመሆኑ በእርሱ ላይ ለመነጋገር ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ - በኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር
አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ - በኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር
`
የግብፅ ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ አቋም ደስተኛ አለመሆናቸውን እየገለፁ ነው፡፡ እንዲያውም ግብፅ የውኃ ሃብትና የመስኖ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን በግትረኝነት ሲከስሱ ተደምጠዋል፡፡ ኅዳሴ ግድብን አስመልክቶ አዲስ አበባ ያለመግባባት ምንጭ የሆኑ ጉዳዮችን ለመፍታት ዝግጁ ሆና ወደ ድርድር ለመመለስ ካልፈለገች በስተቀር ወደ ኢትዮጵያ አልሄድምም ብለዋል፤ ለመደራደር ማለት ነው፡፡

ሚኒስትሩ አብደል ሙታሊብ አል ማስሪ አል ዩም ለሚባል የኢንተርኔት ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ ለሦስቱ ሃገሮች “ለጋራ ጥቅሞቻችን የታሰቡ” ያሏቸውን ሃያ ደረጃዎችን ማለፋቸውን ገልፀው “ኢትዮጵያ ግን አንዳችም እርምጃ አልተራመደችም” እያሉ ይከስሳሉ፡፡ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ግን ከዚህ ጋር አይስማሙም፡፡ እንዲያውም ተቃራኒውን ነው የሚናገሩት “ይልቅ እኛ ነን ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረግን ያለነው፤ ግብፅ ካለችው ሁሉ አንዳችም እርምጃ አልተንቀሣቀሰችም” ይላሉ፡፡
አባይ
አባይ

ግብፃዊው የውኃ ሚኒስትር ለኢትዮጵያ ሕዝብ በቀጥታ ባስተላለፉት መልዕክት “እኛ ከእናንተ ጋር ተቀናቅነን አናውቅም አንቀናቀንምም፡፡ ግብፅ በኅዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ያላት አቋም እናንተን ለመቃወም አይደለም፡፡ በአካባቢያዊም ሆነ በዓለምአቀፍ ደረጃ እያንዳንዱ በሚገነዘባቸው ተጨባጭ ዕይታ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤ በኢትዮጵያ በኩል በቂ የቴክኒክ ጥናቶች ካለመደረጋቸው፣ ለልማት ወይም የሦስቱን የምሥራቅ ናይል ተፋሰስ ሃገሮች፤ ግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያን የውኃ ፍላጎቶች ላለመጉዳት ዝግጁ ካለመሆኗ፤ ግድቡ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሃብት ላይ ካሉት ሪስኮች በተጨማሪ…” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ግድቡን ለመሥራት የገንዘብ ችግር ያለባት መሆኗንም የጠቆሙት ሚኒስትር አብደል ሙታሊብ ግብፅ በቴክኒካዊ፣ በሕግና በፖለቲካ አቋሟ ዕምነት እንዳላት በአፅንዖት ተናግረው “ኢትዮጵያ ግን - ከግብፅ ጋር - በሃሣብ ለመገናኘት አልፈለገችም” ብለዋል፡፡

ምንም እንኳ የግብፁ ሚኒስትር ኢትዮጵያን በግትረኝነት ከስሰው አዲስ አበባ እንደማይሄዱ ይናገሩ እንጂ አቶ ፈቅአሕመድ ግን ቀን አይቆረጥ እንጂ ወገኖቹ እንደገና ለመገናኘት ተነጋግረው ነው የተለያዩት፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የግብፅ የሽግግር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃዘም ኤል-ቤብላዊ አህራም ኦንላይን ለተባለ የኢንተርኔት መገናኛ ብዙኃን ትናንት ሲናገሩ ከኢትዮጵያ ጋር በግዙፉ ግድቧ ላይ የያዝነው ንግግር ወደ ፊት መግፋት ቢያቅተውሙ አልተቋረጠም ወይም አልተቋጨም ብለዋል፡፡

“ምንም ዓይነት ድርድር በአንድ ዙር ተጠናቅቆ አያውቅም” - ብለዋል የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር፡፡ “አንዳንድ ጉዳዮች ግን በድርድሮቹ መሃል መንገድ ላይ ተደንቅረዋል” - ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤብላዊ አክለዋል፡፡
የኅዳሴ ግድብ ማሣያ
የኅዳሴ ግድብ ማሣያ

የግብፅ የመስኖ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ከትናንት በስተያ ሰጥተውት በነበረ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት የግድቡን 30 ከመቶ አጠናቅቄአለሁ የሚለው የመገናኛ ብዙኃን ፍጆታ ብቻ ነው ይበሉ እንጂ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ግን የግድቡ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ እና በተያዘው መርኃግብር መሠረትም እየተከናወነ መሆኑን በየወቅቱ ሲገልፁ ይሰማሉ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG