ዋሺንግተን ዲሲ —
ግብጽ እአኤ በ2013 በአንድ ወታደራዊ ነቁጣ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል ያለቻቸውን 15 እስላማዊ አማፅያንን በሥቅላት ሞት ቀጣች።
እአኤ በ2015 ሥድስት ጂሃዲስቶች በሥቅላት ከተቀጡ ወዲህ ይህ የዛሬው የሞት ቅጣት፣ ግብጽ ውስጥ ከፍተኛው ሲሆን፣ የተፈፀመውም ሰሜን ካይሮ ላይ በሚገኙ በሁለት እሥር ቤቶች ውስጥ መሆኑ ታውቋል።
ባለፈው ወር በሲናይ መስጂድ ከ3መቶ ሕዝብ በላይ ከተገደሉ ወደዚህ፣ የግብጹ ፕሬዚደንት አብድል ፋታህ አል፡ሲሲ፣ "እስላሚዊ መንግሥት ነኝ" በሚለው አማፂ ቡድን ላይ ከፍተኛና ልዩ ጥበቃ እንዲካሄድ ማዘዛቸው ታውቋል።
ማዕከሉን ሲናይ ውስጥ ያደረገው እስላማዊው ነውጠኛ ቡድን፣ ለዓመታት፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖሊስ አባላትን፣ ወታደሮችንና ሲቪሎችን ሲገድል እንደነበር ታውቋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ