በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ኅብረት የኢቦላ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ


ለኢቦላ የተጋለጡና የኢቦላ ታሪክ ያላቸው የአፍሪካ ሃገሮች
ለኢቦላ የተጋለጡና የኢቦላ ታሪክ ያላቸው የአፍሪካ ሃገሮች

የአፍሪካ ኅብረት ምዕራብ አፍሪካን እያመሰ ላለው የኢቦላ ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት ያስችላል የተባለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ አድርጎ በተጎዱት ሃገሮች ላይ የተጣሉት የጉዞና ሌሎቹም ዕገዳዎች ሁሉ እንዲነሱ ወስኗል፡፡

የአፍሪካ ኅብረትና ኢቦላ
የአፍሪካ ኅብረትና ኢቦላ

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:33 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የአፍሪካ ኅብረት ምዕራብ አፍሪካን እያመሰ ላለው የኢቦላ ወረርሽኝ ምላሽ ለመስጠት ያስችላል የተባለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ አድርጎ በተጎዱት ሃገሮች ላይ የተጣሉት የጉዞና ሌሎቹም ዕገዳዎች ሁሉ እንዲነሱ ወስኗል፡፡

ስብሰባውን የጠሩት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶ/ር ንኮሣዛና ድላሚኒ ዙማ “ከኢቦላ ከራሱ ይልቅ በሃገሮቹ ላይ የተጣሉት የጉዞ ዕገዳና ድንበሮችን የመዝጋት እርምጃዎች ሰዉን ይበል እየጎዱት ነው” ብለዋል፡፡

አይሮፕላን ተሣፋሪዎች የኢቦላ ቫይረስ ፍተሻ ሲደረግላቸው
አይሮፕላን ተሣፋሪዎች የኢቦላ ቫይረስ ፍተሻ ሲደረግላቸው

በሌላ በኩል ደግሞ የአፍሪካ ኅብረት መቶ ሐኪሞች፣ ነርሶች፣ ፋርማሲስቶችና ሌሎችም አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ወደተጎዱት የምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች ለመላክ ወመሰኑም ታውቋል፡፡

የመከላከያ ልብሶች ዕጥረት ሥጋት የፈጠረ ቢሆንም አቅርቦቱ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጉዳይ ይዋጣል በተባለው ልገሣ ውስጥ እንደሚካተት ተገልጿል፡፡

ለዚሁ አጠቃላይ ዘመቻ የዩናይትድ ስቴትሰ መንግሥት 35 ሚሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል የገባ ሲሆን የአውሮፓ ኅብረት 115 ሚሊየን ዩሮ፣ እንዲሁም የአፍሪካ ልማት ባንክ 60 ሚሊየን ዶላር ለመለገስ ቃል መግባታቸውና የተወሰነው ገንዘብም በእጅ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

“ይህንን ባለበት ለመቆጣጠር ይቻል የነበረና በጤና መዋቅሮች መዳከም ምክንያት የተስፋፋው” ያሉትን የኢቦላን ቀውስ ለማስቆም ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ሊረባረብ እንደሚገባ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አሳስበዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ “ሚት ዘ ፕሬስ” ለሚባለው የኤንቢሲ ቴሌቪዥን አውታር ትናንት በሰጡት ቃል የዩናይትዩ ስቴትስን ወታደራዊ አቅሞች ኢቦላን ለመቆጣጠር ጉዳይ ሊውል እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ኢቦላን የመዋጋቷን ነገር “የብሄራዊ ደኅነንቷ ቅድሚያ አድርገው ልትወስደው ይገባል” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ አክለው፡፡

ዝርዝር ዘገባ በምሽቱ የጤና ዝግጅታችን ይቀርባል፡፡

XS
SM
MD
LG