አዲስ አበባ - ዋሺንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያ ውስጥ ኢቦላ እስከአሁን እንደሌለ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አቤል የሻነህ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ይሁን እንጂ በተለያዩ ቋንቋዎች የተሰናዱ ተጨማሪ የቅስቀሣ ቁሳቁስ ሕትመት መጠናቀቁንና ወደ ክልሎች ለማከፋፈል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ወደ ምዕራብ አፍሪካ የዘመቱ የጤና ባለሙያዎችም የሁለት ሣምንታት ሥልጠና አጠናቅቀው በየሙያቸው ለመሠማራት እየተዘጋጁ መሆናቸውን አቶ አቤል አመልክተዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡